በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው የCPHIA 2026 የአፍሪካ ህብረተሰብ ጤና ጉባኤ ተጠናቀቀ።
በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው የCPHIA 2026 የአፍሪካ ህብረተሰብ ጤና ጉባኤ ተጠናቀቀ።
“የአፍሪካ የጤና ደህንነት እና ሉዓላዊነት፤ ከጤና ጥገኝነት እና ተጋላጭነት ወደ ባለቤትነት እና ጽናት የሚደረግ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል፣ በአዲስ አበባ የተዘጋጀው የCPHIA 2026 ጉባኤ በስኬት ተጠናቅቋል።
የአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ ዋና ከተማ በሆነችው አዲስ አበባ ከ30 ሺህ በላይ ጉባኤተኞች የተሳተፉበት 5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና ጉባኤ (CPHIA 2026) በማስተናገድ ዳግም የአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ማዕከልነቷን አስመስክራለች።
አፍሪካ የጤና ሉዓላዊነቷን በራሷ አቅም፣ በተቀናጀ ሥርዓትና በዘላቂ ፋይናንስ ማረጋገጥ ይገባታል ያሉት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ እንደገለጹት፣ ባለፉት አምስት ቀናት በተካሄዱ ከ90 በላይ የውይይት መድረኮች የሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ሳይንቲስቶች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የግሉ ዘርፍ ተወካዮችና የሲቪል ማኅበራት ተሳትፈዋል።
በዚህም አፍሪካ በአንድ ድምፅ መናገር መቻሏንና ከጥገኝነትና ተጋላጭነት ወደ ባለቤትነትና ጽናት መሸጋገር የመላው አህጉሪቱ የጋራ ግብ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በ2026 የአፍሪካ ህብረተሰብ ጤና ጉባኤ (CPHIA 2026) የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው በኢትዮጵያ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አነሳሽነትና አመራር እየተከናወኑ ያሉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ጤና ሥራዎች በጤናው ዘርፍ ተጨባጭና ጠንካራ ውጤቶችን እያሳዩ መሆኑን ገልፀዋል።
እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ሰው ሰራሽ አስተውሎትንና ዲጂታል ጤናን መጠቀማችን የታካሚዎችን መረጃ በተሻለ ሁኔታ ለማደራጀት፣ የጤና ስጋቶችን ቀድሞ ለመለየት፣ እንዲሁም ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እያገዘን ነው።
ይህም አፍሪካ እንዴት ጠንካራ የጤና ሥርዓቶችን መገንባትና የራሷን የጤና የወደፊት ዕጣ ፈንታ በባለቤትነት መምራት እንደምትችል ያሳያል ብለዋል።
ከተማችን ከአጋር አካላት ጋር በመሆን አዳዲስ የከተማ ጤና ሐሳቦችን ለመሞከርና ተግባራዊ ለማድረግ ሁልጊዜም ክፍት ናት። እርስ በርስ በመደጋገፍ፣ እውቀትን በመጋራትና ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት፣ በመላው አህጉራችን ለሚመጡት ትውልዶች ዘላቂ መሠረት መጣል እንችላለን።
በጤናው ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የልማት መሠረቶች ላይ በቅርበት አብረን እንድንሠራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
እንደ ሀገራችን ሆነ፣ እንደ ከተማችን አዲስ አበባ፣ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ30 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የታደሙበትን ትልቅ ኮንፈረንስ በብቃት አስተናግዳለች።
እነዚህን ከ30 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ለተከታታይ 6 ቀናት በአዳራሽ ብቻ ሳይሆን፣ በከተማችን የተለያዩ ቦታዎች እየተዟዟሩ ጐብኝተዋል። ቀን ብቻ ሳይሆን፣ ምሽትና ሌሊትም በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በነፃነት እየተዟዟሩ ሲዝናኑ ተመልክተናል፤ እነሱም ስለከተማችን ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
በዚህም ትልልቅ አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን በብቃት ማስተናገድ እንደምንችል በተግባር አሳይተናል።
በመሆኑም ይህን ታላቅ ኮንፈረንስ ላዘጋጀው የአፍሪካ CDC ከልብ አመሰግናለሁ። እንዲሁም ኮንፈረንሱን በዋናነት ላስተባበረው የጤና ሚኒስቴር እንዲሁም እንግዶችን በመቀበልና በማስተናገድ፣ በትራንስፖርት፣ በሆቴል፣ በውሃ፣ በመብራት፣ በአዳራሽ አገልግሎት፣ በጸጥታ፣ በማስጎብኘት፣ በጽዳትና በሌሎችም ዘርፎች የተሳተፉ ሁሉም ተቋማትና የሥራ ኃላፊዎች ታላቅ ምስጋና ይገባቸዋል።
ይህ ስኬት አዲስ አበባ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን በብቃት፣ በጥራትና በኃላፊነት ማስተናገድ የምትችል ከተማ መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ ነው።
አዎ፣ እንችላለን!
ለመጀመሪያ ጊዜ ከ30 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን በብቃት አስተናግደናል፤ በሚቀጥለው ዓመትም ለCOP32 ከ100 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን በብቃትና በጥራት ለማስተናገድ እየተዘጋጀን ነው።
ከአሁኑ ጀምሮ ልዩ ትኩረት እንስጥ፤ በእጃችን ያሉትን ሥራዎች በጊዜ፣ በጥራትና በብቃት እንፈጽም። ይህን ታላቅ እድል በምንም መልኩ ሳናባክን፣ የኢትዮጵያን የእንግዳ ተቀባይነት፣ የፈጠራ አቅምና የሥራ ትጋት ለዓለም የምናሳይበትን ታላቅ ዕድል በተግባር እናሳካ።
COP32ን ውጤታማ፣ የማይረሳ እና የኢትዮጵያን አቅም የሚያሳይ ታላቅ ዓለም አቀፍ ዝግጅት ለማድረግ፣ ዛሬ በትጋት እንሥራ። ዓለምንም በመዲናችን እናስተናግድ፤ ኢትዮጵያንም በኩራት እናሳይ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን
ና ህዝቦቿን ይባርክ!
As the capital of our country, Addis Ababa has successfully hosted, for the first time in our history, a major international conference attended by more than 30,000 participants.
For six consecutive days, participants experienced not only the conference venues but also different parts of our city. They explored Addis Ababa during the day and enjoyed its streets, hospitality, and vibrant atmosphere in the evenings and at night. Their positive feedback demonstrated that our city is capable of hosting major continental and international events with confidence and professionalism.
This achievement was made possible through the leadership and coordination of the Africa CDC and the Ministry of Health, alongside the dedicated efforts of all institutions and professionals responsible for transportation, accommodation, water and electricity, conference venues, security, tourism, cleaning, hospitality, and other essential services. I extend my sincere appreciation to all those whose collective efforts made this success possible.
Yes, we can!
We have successfully hosted more than 30,000 participants, and next year, for COP32, we are preparing to welcome more than 100,000 participants with even greater capacity, quality, and excellence.
Let us give this opportunity the attention it deserves. Let us complete every task before us on time and to the highest standards. Most importantly, let us turn this opportunity into a platform to showcase Ethiopia’s hospitality, capacity, creativity, and potential to the world.
Let us work with greater determination from today to make COP32 a successful and unforgettable global event—one that puts Addis Ababa and Ethiopia on the world stage and leaves a lasting legacy.
Let us welcome the world to our capital and show what Ethiopia can achieve!
May God bless Ethiopia and its people!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.