የኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድስ 100ኛ ዓመት የዲፕ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድስ 100ኛ ዓመት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ምክንያት በማድረግ ልዩ የብስክሌት ውድድር በአዲስ አበባ ተካሄደ።

በአጭር ጊዜ በአዲስ አበባ እየተገነቡ ያሉት መሰረተ ልማቶች የነዋሪዎችን መሰረታዊ ፍላጎቶች የሚመልሱ ናቸው፡- በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ አምባሳደር ክሪስቲን ፒረን

የኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድስ 100ኛ ዓመት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ምክንያት በማድረግ ልዩ የብስክሌት ውድድር በአዲስ አበባ ተካሄደ።

ይህ ታላቅ የወዳጅነት መርሐ ግብር የተካሄደው በቅርቡ በከተማዋ በተገነቡ የኮሪደር ልማት ውበት በተላበሰችው አዲስ አበባ እና በተለይም ዘመናዊ የብስክሌት ባህል እንዲዳብር እና ለነዋሪዎች ምቹ የእንቅስቃሴ ሥፍራ እንዲፈጠር ታስበው በተገነቡት ዘመናዊ የብስክሌት መንገዶች ላይ ነው።

መንገዶቹ ለከተማዋ ውበት ከመስጠት ባለፈ፣ የአረንጓዴ ትራንስፖርት አማራጮችን ለማስፋፋት እና ዓለም አቀፍ የስፖርትና የወዳጅነት ኩነቶችን ለማስተናገድ ያላቸውን ፋይዳ በተግባር ያሳዩ ናቸው።

በአዲስ አበባ እየተገነቡ ያሉት መሰረተ ልማቶች የነዋሪዎችን መሰረታዊ ፍላጎቶች የሚመልሱና የነዋሪዎች ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ናቸው ።

የብስክሌት ጉዞ በኔዘርላንድ ባህል ውስጥ ትልቅ ሥፍራ ያለው የዕለት ተዕለት የሕይወት ዘይቤ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ይህ ውድድር በአዲስ አበባ በተገነቡት አዳዲስ የብስክሌት መንገዶች ላይ መካሄዱ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የባህል ልውውጥ ከማሳደጉም በላይ፣ ከተማዋ እየገነባች ያለችውን ጤናማና ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ የትራንስፖርት ባህል የሚያበረታታ ነው።

በውድድሩ ላይ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ የኔዘርላንድስ ዲፕሎማቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.