በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ12 ክላስተሮች...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ12 ክላስተሮች ተደራጅቶ እየተተገበረ የሚገኘው የ90 ቀናት ዕቅድ የመጀመሪያዎቹ 45 ቀናት አፈጻጸም በጥልቀት ተገምግሟል።

በግምገማውም ጥሩ ውጤት የተመዘገበባቸውን ሥራዎች ይበልጥ በማጠናከር፣ ልዩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በፍጥነት ለመፍታትና በተጠናከረ ክትትል ወደ ተግባር ለማሸጋገር በቅንጅትና በትጋት መሥራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በቀጣይም የእያንዳንዱ ክላስተርና ክፍለ ከተማ የሥራ አፈጻጸም በየወሩ እየተገመገመና በቀጣይነት እየተከታተለ ዕቅዱ በተጨባጭ ውጤት እንዲተረጎም የሁሉም አመራርና ፈጻሚዎች የተቀናጀ ርብርብ እንዲጠናከር አቅጣጫ ተሰጥቷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.