የህዳር 2019 ዜና መፅሔት
የነዋሪዎችን የኑሮ ጫና በተግባር የሚቀንሱ የገበያ ማዕከላት
በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በቀጥታ ለሸማቾች የሚቀርቡባቸውን የገበያ ማዕከላትንና የቅዳሜና ዕሁድ ገበያዎች ተደራጅተዋል።
በእነዚህ ማዕከላት ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ፍጆታቸዎች በሚያገኙበትአቅራቢያ ያለአስፈላጊ
የጉዞ ወጪና የጊዜ ብክነት፣ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት እየቻሉ ነው።የአሠራሩ ዋነኛ ጥንካሬ ትኩስ ምርትን ከአምራቹ በቀጥታ ወደ ሸማቹ ማድረስ መቻሉ ነው። በዚህም በምርት አቅርቦትና በሸማች መካከል የሚገቡ አላስፈላጊ የደላላ ሰንሰለቶችን በማሳጠር፣ የዋጋ መናርን ለመቀነስና ሸማቹ በተሻለ ዋጋ ምርት እንዲያገኝ ዕድል ተፈጥሯል።
ይህ አሠራር ሸማቹን ብቻ የሚጠቅም ሳይሆን አምራቹም ምርቱን በቀጥታ ለገበያ በማቅረብ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ ያስችለዋል።
በዚህም የአምራችና የሸማች ትስስርን ከማጠናከር ባሻገር፣ የከተማና የገጠር ኢኮኖሚያዊ
ከሁሉም በላይ እነዚህ የገበያ ማዕከላት የኑሮ ውድነትን በንግግር ብቻ ለመቋቋም ሳይሆን፣ የምርት አቅርቦትን በማሳደግ፣ የገበያ ትስስሩን በማሻሻልና ሸማቹን በቀጥታ በመደገፍ በተግባር መፍትሄ የሚያመጡ ናቸው።
ለብዙ ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ወጪን ለማቃለል እውነተኛና ተደራሽ የገበያ አማራጭም ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቋም ግልጽ ነው፤ የነዋሪዎችን የኑሮ ጫና የሚቀንሱ፣ የገበያ ተደራሽነትን የሚያሰፉና የምርት አቅርቦትን የሚያረጋግጡ ተግባራዊ መፍትሄዎችን ማጠናከር ነው።
ለሸማቹ ህብረተሰባችን የቀረቡ 282 የሰንበት ገበያዎች
ባለፉት አምስት ዓመታት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እና በሰው ህይወት ላይ ተጨባጭ ለዉጥ ያመጡ በርካታ ሰዉ ተኮር ተግባራትን በማከናወን የከተማዋን ሁለተናዊ እድገት ማረጋገጥ ተችሏል ።
ከተማን ማልማት ከመሰረት ልማት እድገት ባሻገር ሰዉ ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባራት ላይ መስራት መሆኑን የተረዳው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመዲናችን አዲስ አበባ የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት ጫና ለማቅለልና ገበያውን ለማረጋጋት በአምስቱም የከተማዋ መግቢያ በሮች አጅግ ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት በመገንባት በሸማቹ ማህበረሰብ ዘንድ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት ተችሏል።
በተለይም መንግስት የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ከ282 በላይ የሰንበት ገበያዎች ለነዋሪው ቅርብ በሆኑ አካባቢዎችና በሁሉም ክፍለ ከተሞች በማስፋፋት እንዲሁም የበጀት ድጎማ በማድረግ መሰረታዊ ሸማች የህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀትና በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ እንዲሆኑ በማድረግ በከተማዋ ጥራት ያለዉ ምርት በስፋት እንዲቀርብ እና የዋጋ መረጋጋት እንዲሰፍን ማድረግ ችሏል፡፡
በነዚህ የገበያ ማዕከላት ምርት እና ምርታማነትን በመጨመር ፣ የምርት አቅርቦትን በማሳደግ፣የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር እና የደላሎችን ሰንሰለት በመበጣጠስ እንዲሁም በኬላዎች የሚስተዋለዉን ያልተገባ ክፍያን በመስቆም በሻጭና በሸማች መካከል ቀጥታ ግንኙነት እንዲፈጠር ማድረግ ተችሏል፡፡
በአጠቃላይ እነዚህ በመዲናችን የተገነቡ ዘመናዊ የገበያ ማእከላትና የቅዳሜና ዕሁድ ገበያዎች አዲስ አበባን ከአጎራባች ከተሞች ጋር በማስተሳሰር የተለያዩ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርት ዉጤቶች በተመጣጣኝ እና የሸማቹን ኪስ በማይጎዳ መልኩ በስፋት እና በጥራት በማቅረብ ፣አርሶ አደሩን ጨምሮ የከተማዋ ሸማችና አምራች ቀጥታ በማገናኘት ፍትሃዊ የግብይት ስርዓት በማስፈንሁለተናዊ ትሩፋቶች መሆናቸውን ማሳያ ናቸው።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.