ታሪክን በልማት ማስቀጠል፤ አሻራን ለትውልድ ማስተላለፍ!
ታሪክን በልማት ማስቀጠል፤ አሻራን ለትውልድ ማስተላለፍ!
ከተማ የምትገነባው በመንገድና በሕንፃ ብቻ አይደለም፤ ታሪኳን የሰሩ፣ ለሀገር ውለታ የዋሉ ባለውለታዎቿን በክብር በማስቀጠልም ጭምር ነው።
በአደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ የኢትዮጵያንና የአፍሪካን ስፖርት በማሳደግ ታላቅ አሻራ ያሳረፉትን ይድነቃቸው ተሰማን የሚዘክር ሐውልት መገንባታችን ከዚህ እሳቤ የተነሳ ነው።
ይድነቃቸው ተሰማ የአፍካ እግር ኳስ አባት፤ ይገባዋል!!
እንደዚሁም ለሀገርና ለትውልድ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ታላላቅ ሰዎችን መዘከር ታሪክን ከዛሬ ልማት ጋር በማስተሳሰር ለነገ ትውልድ ኩራትና መነሳሻ ይፈጥራል።
ልማት የዛሬን ከተማ ብቻ አይገነባም፤ የነገን ታሪክም ይጽፋል።
ታሪክን እያከበርን፣ ማንነትን እያጠናከርን፣ አሻራን ለትውልድ እያስተላለፍን እንቀጥላልን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
Preserving History Through Development; Inspiring Future Generations!
A city is built not only through infrastructure but also by honoring its history and those who shaped its legacy.
The monument honoring Yidnekatchew Tessema near Adey Abeba Stadium celebrates his remarkable contribution to Ethiopian and African football.
The Father of African Football deserves a lasting place in our city’s history!
Development builds our cities; preserving history strengthens our identity and inspires generations to come.
May God bless Ethiopia and its people.
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.