ዛሬ ከወርልድ ባንክ ግሩፕ ጋር ያለንን የረጅም ጊዜ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ያለመ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።
እስከአሁን በከተማ የውሃ አቅርቦት መሠረተ ልማት ማስፋፊያና ማሻሻያ፣ በፍሳሽ መሰብሰቢያና ማጣሪያ ተቋማት ግንባታ፣ እንዲሁም በትራንስፖርትና በሌሎች ቁልፍ የልማት ዘርፎች ከወርልድ ባንክ ግሩፕ ለተገኘው ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን።
በቀጣይም ትብብራችንን በማስፋት፣ አዳዲስ የጋራ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና በመተግበር ለከተማችን ዘላቂ ልማትና ለነዋሪዎቻችን የተሻለ ኑሮ በጋራ ለመሥራት ጥሩ ውይይት አድርገናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.