የነዋሪዎችን የኑሮ ጫና በተግባር የሚቀንሱ የገበ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የነዋሪዎችን የኑሮ ጫና በተግባር የሚቀንሱ የገበያ ማዕከላት!

በከተማችን አዲስ አበባ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ፍጆታ በተመጣጣኝ ዋጋ ማሟላት የሚያስችል ሁኔታ እየተመቻቸ ነው።

ይህንን መርህ በተግባር የሚያሳየው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በቀጥታ ለሸማቾች የሚቀርቡባቸውን የገበያ ማዕከላትንና የቅዳሜና ዕሁድ ገበያዎች ተደራጅተዋል።

ከ282 በላይ የቅዳሜና ዕሁድ ገበያዎች መዘርጋታቸው የዚህ ጥረት አንዱ ጉልህ ውጤት ነው። በእነዚህ ማዕከላት ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ፍጆታቸዎች በሚያገኙበት አቅራቢያ፣ ያለአላስፈላጊ የጉዞ ወጪና የጊዜ ብክነት፣ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት እየቻሉ ነው።

የአሠራሩ ዋነኛ ጥንካሬ ትኩስ ምርትን ከአምራቹ በቀጥታ ወደ ሸማቹ ማድረስ መቻሉ ነው። በዚህም በምርት አቅርቦትና በሸማች መካከል የሚገቡ አላስፈላጊ የደላላ ሰንሰለቶችን በማሳጠር፣ የዋጋ መናርን ለመቀነስና ሸማቹ በተሻለ ዋጋ ምርት እንዲያገኝ ዕድል ተፈጥሯል።

ይህ አሠራር ሸማቹን ብቻ የሚጠቅም ሳይሆን አምራቹም ምርቱን በቀጥታ ለገበያ በማቅረብ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ ያስችለዋል።

በዚህም የአምራችና የሸማች ትስስርን ከማጠናከር ባሻገር፣ የከተማና የገጠር ኢኮኖሚያዊ ትስስርንም አሳድጓል።

ከሁሉም በላይ እነዚህ የገበያ ማዕከላት የኑሮ ውድነትን በንግግር ብቻ ለመቋቋም ሳይሆን፣ የምርት አቅርቦትን በማሳደግ፣ የገበያ ትስስሩን በማሻሻልና ሸማቹን በቀጥታ በመደገፍ በተግባር መፍትሄ የሚያመጡ ናቸው።

ለብዙ ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ወጪን ለማቃለል እውነተኛና ተደራሽ የገበያ አማራጭም ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቋም ግልጽ ነው፤ የነዋሪዎችን የኑሮ ጫና የሚቀንሱ፣ የገበያ ተደራሽነትን የሚያሰፉና የምርት አቅርቦትን የሚያረጋግጡ ተግባራዊ መፍትሄዎችን ማጠናከር ነው።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.