በአምስት ዓመታት ውስጥ ቤቶችን ገንብተን ለማስረ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአምስት ዓመታት ውስጥ ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ ለሕዝባችን ቃል ገብተናል፤ ይህንንም ቃላችንን በተግባር ለማረጋገጥ ቀን ከሌት ያለ እረፍት እየተጋን እንገኛለን። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሕዝባችን በመኖሪያ ቤት እጥረት ምክንያት የሚገጥመውን ፈተናና ስጋት በሚገባ እንረዳለን፤ ደረጃቸውን የጠበቁና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ መኖሪያ ቤቶችን ማመቻቸት የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን፣ ለዜጎቻችን ያለብን አደራና ኃላፊነት መሆኑንም ጠንቅቀን እንገነዘባለን።

ዋነኛ ትኩረታችን ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ፣ የሕዝባችንን የመኖሪያ ቤት ጫና ማቃለል እና በመላው አገሪቱ ለሚገኙ ቤተሰቦች የተሻለ የኑሮ ምዕራፍ መክፈት ነው።

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ቃልን በተግባር !

ከጉባ ብስራቶች አንዱ እንደ ሀገር በአምስት ዓመታት ውስጥ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለዜጎቻችን ለማስረከብ የገባነው ቃል ነው።

እንደ አዲስ አበባም በ21 ሳይቶች 100 ሺህ ቤቶችን እየገነባን ነው። እነዚህም 50 ሺህ በከተማው በጀት፣ 50 ሺህ ደግሞ በመንግሥት–የግል አጋርነትና በማኅበራት እየተገነቡ ነው።

ዛሬም ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በቱሉ ዲምቱ 33 ብሎኮችን እና በአዲስ ከተማ ቅጠል ተራ 9 ብሎኮችን ጎብኝተን ጥሩ አፈፃፀም ላይ መሆናቸውን ተመልክተናል። 

የሕዝባችንን የቤት ጫና ማቃለል ለእኛ የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን አደራና ኃላፊነት በመሆኑ 24/7 ተግተን እንሰራለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.