በዳካር 2026 የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ 5 የወርቅና 3 የብር በድምሩ 8 ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቋ የሚያኮራ ታሪካዊ ውጤት ነው።
ለዚህ ውጤት የበቃችሁ ወጣት አትሌቶቻችንን፣ አሰልጣኞቻችንንና የስፖርቱን ቤተሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ።
በስፖርት ዘርፍ በተለይም ዘመናዊና ተደራሽ የስፖርት መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት፣ የታዳጊ ወጣቶችን ተሰጥኦ በማውጣትና በማብቃት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮች የነበራትን ከፍተኛ ቦታ ዳግም እንድትይዝ የተጀመረው ሥራ በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል።
የዛሬዎቹ ድሎች የነገዋ ታላቅ ኢትዮጵያ መሠረቶች ናቸው።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.