ዛሬ ከCOP31 መድረክ ጎን ለጎን፣ ከህፃናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኬት ሃምፕተን ጋር ገንቢ ውይይት አድርገናል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሃምፕተን ጋር ኢትዮጵያ የCOP32 አዘጋጅ ሀገር እንደመሆኗ በትብብር ዕድሎች፣ እንዲሁም በቆሻሻ አያያዝና አጠቃቀም ፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋምና የከተሞች ትብብርን በማጠናከር ዙሪያ ተወያይተናል።
ዘላቂ፣ አረንጓዴና አካታች የከተማ ልማትን ለማረጋገጥ ያለንን ትብብር ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር ለዛሬውና ለመጪው ትውልድ የተሻለችና ዘላቂ ከተማ ለመገንባት በቁርጠኝነት እንሠራለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.