ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ጋር ከC...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ጋር ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ቀደም ብሎ ተገናኝተናል።

በሶማሊያ ወቅታዊ የደኅንነት ሁኔታና ሰፋ ባሉ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሃሳቦችን ተለዋውጠናል።

‎ የቀጣናውን ሰላም እና መረጋጋት ለማስፈን ቀጣይነት ያለው ውይይትና ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተናል።

ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከኢራቁ ፕሬዝዳንት ኒዛር አሚዲ ጋር መክረናል።

‎የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እንዲሁም በልማት ትብብር ረገድ የጋራ አቅም ያላቸውን ዘርፎች ወደ ውጤት የመቀየር ስራዎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።‎

‎በተጨማሪም በኢትዮጵያ የልማት ውጥኖችና በጋራ ፍላጎት ላይ በተመሰረቱ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ የተለዋወጥን ሲሆን፣ በተግባር ላይ ለተመሰረተ ትብብር ጠንካራ ትስስር መገንባት ያለውን አስፈላጊነት በትኩረት ተመልክተናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.