በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ጋር በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።
በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ጋር በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።
በአቪዬሽን ትብብር እና የኢትዮጵያን የCOP32 ፕሬዝዳንትነት ለመደገፍ በሚደረገው አጋርነት ላይ የመከርን ሲሆን፣ የጋራ ፍላጎቶችን መሠረት በማድረግ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ይበልጥ ለማስፋት እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የወል ጉዳዮች ወደ ተጨባጭ ውጤቶች ለመቀየር የሚያስችል ፍሬያማ ምክክር አድርገናል።
ከፊንላንድ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ተገናኝተን መክረናል።
ከዚህ በፊት በG20 ጉባኤ ወቅት ባካሄድነው የሁለትዮሽ ስብሰባችን ወቅት የተደረጉ ውይይቶችን ተግባራዊነት የተመለከተ ውይይት አድርገናል።
በዋና ዋና ዓለም አቀፍ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች፣ በቀጣናዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች እና በጋራ ፍላጎቶችን በውይይታችን የተመለከትን ሲሆን፤ ይህም ፊንላንድ ኢትዮጵያ የምትረከበውን የCOP32 ፕሬዝዳንትነት ድጋፍ ጨምሮ፣ የጋራ መግባባት የተደረሰባቸውን ዘርፎች ቀጣይነት ባለው ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ልዩ ትኩረት የሰጠንበት ነው።
ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል።
በውይይታችንም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ያለውን ትብብር ማሳደግ፣ በኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ማበረታታት እና ኖርዌይ ኢትዮጵያ ለምትረከበው የCOP32 ፕሬዝዳንትነት የምታደርገውን ድጋፍ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ መክረናል።
ውይይታችን ሰፊ የሁለትዮሽ ትብብርን ጨምሮ በወቅታዊ፣ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሃሳብ ልውውጥ የተደረገበት ሲሆን፣ ይህም በተግባራዊ የትብብር መስኮች ወደፊት ለመራመድና አጋርነታችንን ይበልጥ ለማጠናከር ያለንን የጋራ ፍላጎት ያንጸባረቀ ነው።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.