ከUN-Habitat ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር ባደረግነው ውይይት፣ በአዲስ አበባ የከተማ ለውጥና ዘላቂ ልማት ዙሪያ ያለንን ትብብር ለማጠናከር ተነጋግረናል።
ከተማችን በሻንጋይ በተካሄደው የዓለም የከተሞች ቀን ያገኘችውን የዘላቂ የከተሞች ልማት ሽልማትና በሴኡል የተሰጣትን የስማርት ከተማ ዕውቅና በማስመልከት፣ የUN-Habitat ዋና ደይሬከተር እንኳን ደስ አላችሁ ያሉን ሲሆን፣ እኛም ምስጋናችንን ገልጸናል።
በቀጣይም በከተማ ልማትና ፕላን ያለንን ትብብር በማጠናከር፣ ቀጣዩን የዓለም የከተሞች ቀን በአዲስ አበባ በስኬት ለማክበር በቅንጅት ለመሥራት ተስማምተናል።
በቅርቡ የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ወደ ተግባር ለማሸጋገርም የጋራ የትግበራና የክትትል ሥርዓት በመዘርጋት፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ፕሮጀክቶች በመለየት ላይ ተወያይተናል።
አዲስ አበባ COP32ን ለማስተናገድ በምትዘጋጅበት ወቅት፣ የUN-Habitat ስትራቴጂያዊና ቴክኒካዊ አጋርነት የከተማችንን የልማት አጀንዳ ለማፋጠንና ዘላቂ ውጤት ለማስገኘት ጠቃሚ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ዓላማችን አጋርነትን ወደ ተግባር፣ ተግባርን ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር ለሕዝባችን ዘላቂ ጥቅም ማስገኘት ነው።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.