ከ200 በላይ የሚሆኑ ሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በትገኙበት አዲስ አበባ በአንታሊያ ልምዷን ታካፍላለች
መዲናችን አዲስ አበባ ባከናወነችው ዘርፈ ብዙ የልማት ስራ ለብዙዎች ተምሳሌት ከተማ መሆን በመቻሏ በተለይም የአየር ንብረትን ለመቋቋም በምታደርገው ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ በርካታ የአለም ሀገራት ልምድ የሚቀስሙባት ሀገር እንድትሆን አስችሏትል፡፡
ለአብነትም በአሳለፍነው አመት በመዲናችን የተካሄደው 2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ACS2) በብቃት በማስተናግድ እና የአየር ንብረት ለውጥ በመቋቋም ከተማዋን ንጹህ ለኑሮ ተስማሚ በማድረግ እና ለአካባቢ ጠንቅ የሆኑ ወንዞችና የወንዝ ዳርቻ ልማቶችን ጤናማ በማድረግ ያከናወነችው ስራ የአለምን ትኩረት እንድታገኝ አስችሏታል ፡፡
በዚህ ተሞክሮ መዲናዋ በCOP31 ጉባኤ ላይ በመሳተፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ያከናወነቻቸውን ተግባራት፣ የአረንጓዴ እና የዘላቂ ልማት እንቅስቃሴዎቿን ከ200 በላይ የሚሆኑ ሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በትገኙበት ልምዷን ታካፍላለች።
በመላው ሀገሪቱ ሚካሄደውን አረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር እንዲሁም በከተማዋ የተከናወኑ የኮሪዶር እና የወንዝዳር ልማት ፕሮጀክቶች፣ የሰው ተኮር ልማት እንዲሁም በወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች አካታችና የተቀናጀ ልማትን ማረጋገጥ ምቹ የእግረኛና የተሸከርካሪ መንገድን መገንባት እና ታዳሽ የተፈጥሮ የትራንስፖርት አማራጭ እና መሰረተ ልማትን በመገንባት ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ የከተማዋ የደን ሽፋን ከዚህ ቀደም ከነበረበት 2 ነጥብ ስምንት በመቶ ወደ 24 በመቶ ለማድረስ ያከናወነችውን ዘርፈ ብዙ ስራ የአለም ሀገራት የሚሳተፉበት እና በርካታ ልምድ የሚቀሰምበትን የCOP 32 ጉባዬ ለማስተናገድ ከሌሎች ሀገራት በተለየ እንድትመረጥ አስችሏታል፡፡
በተለይም ከተማዋን አረንጓዴ በማልበስ ምቹና ለኑሮ ተስማሚ ከባቢን በመፍጠር እና ነፋሻማ ቦታዎችን በመገንባት እና በማስዋብ በነዋሪው ዘንድ አዲስ የአኗኗር ዘይቤን በመፍጠር ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብን የመገንባት ሚና ትኩረት እንድታገኝ አድርጓል ፡፡በተጨማሪም የተፈጥሮ ሀብቶችን መጠቀም የሚያስችል ታሪካዊ የሆነ የኢነርጂ ሽግግር በማድረ የከተማ አውቶብሶችን ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ በመለወጥ ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ለአየር ንብረት ለውጥ ያላትን ቁርጠኝነት ያመላክታል።
በአጠቃላይ አዲስ አበባ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ማዕከልነት፣ ዓለም አቀፍ ተሳታፊዎችን በብቃት የማስተናገድ፣ የሎጂስቲክስና የፀጥታ አቅም እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት (AU) እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትከ (UN) የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ በመሆኗ ምክንያት፣ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን እና ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ስብሰባዎችን የማስተናገድ ረጅም እና የተረጋገጠ ልምድ ያላት በመሆኗ ለኮፕ 32 (የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ) አስተናጋጅነት እንድትመረጥ ትልቅ አበርክቶ አለው፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.