ለሁሉ ተስማሚ የሆነችው አዲስ አበባ ጎዳናዎቿን ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ አድርጋለች
ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ምቹ ያልነበሩ ተሽከርካሪ እና እግረኛ እኩል የሚጋፋባቸው ለአደጋ የተጋለጡ በተለይም በየመንደሩ የሚኖሩ ታዳጊዎች አማራጭ ባለማግኘታቸው ኳስ ለመጫወት የተሽከርካሪን መንገድ የሚሻሙ ነበሩ። ዛሬ ይህ ታሪክ ሆኖ አልፏል ።
ችግሩን የተረዳው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ ለታዳጊዎች ፣ ለወጣቶች እና ለህፃናት ምቹ ከተማን በመፍጠርና ዘመናዊ መንገዶችን በመገንባት ለእግረኛ ለሳይከል እንዲሁም ለተለያ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ ከተማን በመገንባት ዘመን ተሻጋሪ ስራን እየሰራ ይገኛል፡፡
በተለይ በቅርብ ጊዜ የተገነቡ እና ለህዝብ አገልግሎት ክፍት የተደረጉ አዲስ ስፖርት ፓርክ እና አራዳ ፓርክን ጨምሮ በተለያ ክፍለ ከተሞችና ቦታዎች የተሰሩ ዘመናዊ ሜዳዎችና ስፖርት ማዘውተሪያዎች በውስጣቸው የእግር ኳስ የቅርጫት ኳስ ሜዳ ቴንስ እና ሌሎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጊያ ግብዓቶች የተሟሉላቸው ናቸው፡፡
ዛሬ ላይ የአዲስ አበባ ውብ ጎዳናዎች ሁሉን በመልኩ አድርገው በእግረኛና በሳይክል መንገድ ተውበው ፣ በአረንጓዴ አበቦች አጊጠው ለእግር ጎዞዎች እንዲሁም ለተለያዩ ስፖርታዊ እንቅሰቃሴ ምቹ የጤና ማዕከል ሆነዋል።
አሁን ላይ በአዲስ ጎዳናዎች ሲጓዙ በተመቻቸላቸው ጎዳናዎች እና ቦታዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ወጣቶች ፣ ህፃናት፣ አረጋውያን እና ጎልማሶችን መመልከት የተለመደ ባህል ሆኗል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.