አዲስ አበባ፦ የመደመር ጉዞ ውጤትና የአፍሪካ የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ፦ የመደመር ጉዞ ውጤትና የአፍሪካ የለውጥ ተምሳሌት

ለ3 ቀናት ሲካሄድ በቆየው የ2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ (APPS) ማጠቃለያ በኋላ የጉባኤው ተሳታፊ አመራሮች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎች፣ እና አለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

መዲናዋ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያስመዘገበችውን ለውጥ የመደመር ፍልስፍና በተግባር ያመጣውን ውጤት ለመመልከት ዕድል እንደፈጠረላቸውም አንስተዋል። 

ተሳታፊዎቹ የብልፅግና ፓርቲ የመደመር ጉዞ ለኢትዮጵያ ለውጥና እመርታ ጠንካራ መሠረት መጣሉን፣ ይህንንም ተሞክሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በየራሳቸው እውነታና አቅም ተረድተው በመተግበር የአህጉሪቱን ለውጥ ማፋጠን እንደሚችሉ መግለጻቸው የጉብኝቱን ፋይዳ የበለጠ ያጎላዋል።

በተለይም በከተሞች ልማት የተጀመረው ስራ በጣት በሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ በብዙ ከተሞች ላይ ያስገኘው ተጨባጭ ለውጥ አስደናቂ ነው ብለዋል።

 ከተሞች የሰው ልጅ የኑሮ፣ የኢኮኖሚ፣ የፈጠራና የስልጣኔ ማዕከላት እንዲሆኑ የተሰጠው ትኩረት፣ የከተማ ልማትን ከመሠረተ ልማት ግንባታ ባለፈ የዜጎችን የኑሮ ጥራት የሚያሻሽል ሁለንተናዊ የለውጥ ሂደት አድርጎታል።

የአዲስ አበባ ለውጥም የዚህ እውነታ ግልጽ ማሳያ ነው። ከተማችን በመንገድ፣ በወንዝ ዳርቻ ልማት፣ በአረንጓዴ ስፍራዎች፣ በህዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣ በትራንስፖርትና በዘመናዊ የከተማ መሠረተ ልማቶች ያስመዘገበችው እመርታ የለውጡን ስፋትና ጥልቀት ያሳያል። 

ከዚህም ባለፈ አዲስ አበባ ዛሬ የሀገራዊ ለውጥ ተምሳሌት ብቻ ሳትሆን ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞችም የልማት ልምድ የምታካፍል፣ ፈር ቀዳጅ ከተማ ሆናለች።

ይህ ለውጥ የሚያሳየው ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መንግሥት፣ ጠንካራ መንግሥትም ለሀገራዊ ለውጥና ለልማት ወሳኝ መሠረት መሆኑን ነው። 

ብልፅግና ፓርቲ ሰውን ማዕከል ባደረጉ ፖሊሲዎችና በመደመር እሳቤ የሀገርን ውስጣዊ ፀጋዎች፣ የሰው ኃይልና የሀብት አቅም በማስተባበር ለውጥን ከውጭ ከመጠበቅ ይልቅ በራስ አቅም መፍጠር እንደሚቻል በተግባር አሳይቷል።

ከሁሉም በላይ የመደመር ጉዞ ዋና መርህ ሰውን ኑሮ እና አኗኗር ማሻሻል የልማት ዓላማም የልማት ተጠቃሚም ማድረግ ነው። 

የAPPS ተሳታፊዎች ጉብኝት አዲስ አበባ ያስመዘገበችውን ለውጥ የአፍሪካ የጋራ ተሞክሮና የጋራ ዕድገት አካል ለማድረግ ያለውን ዕድል ያጠናክራል።

አፍሪካ ያላትን ፀጋ በማሰባሰብ፣ በጋራ በመሥራት፣ በልምድ በመለዋወጥና በራሷ አቅም በመተማመን የምትፈልገውን የብልፅግና ዕድገት ማረጋገጥ ትችላለች። 

የአዲስ አበባ ለውጥም ይህንኑ የሚያረጋግጥ ተጨባጭ ምስክር ነው።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.