አዲስ አበባ ከተማ የትራንሰፖርት ዘርፉን ወደ ታዳሽ ሃይል በመለወጥ በርካታ ተግባራትን በማከናውን ላይ ትገኛለች:
መዲናችን አዲስ አበባ ከተማ የትራንሰፖርት ዘርፉን ወደ ታዳሽ ሃይል በመለወጥ በርካተ ተግባራትን በማከናወን ላይ ትገኛለች፡፡ በተለይም አዳዲስና በቴክኖሎጂ የታገዙ ዘመናዊ ተሸከርካሪዎችን ወደ ስራ በማስገባት እንዲሁም ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የኢትዮጵያን የሲቪል መሠረት የሚያጠናክር የተፈጥሮ ሀብቶችን መጠቅም የሚያስችል ታሪካዊ የሆነ የኢነርጂ ሽግግር በማድረግ ምሳሌ መሆን ችላለች ፡፡
በዚህ አዲስ ታሪካዊ በሆነ ሽግግር መዲናችን አዲስ አበባ በቅርቡ 26 የከተማ አውቶብሶችን ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ በመለወጥ ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ አዲስ ምዕራፍ ከፍታለች።
ይህ ታሪካዊ ሽግግር የሕዝብ ትራንስፖርትን ወጪ በመቀነስና የአየር ብክለትን በማስቀረት፣ የኢኮኖሚ አቅም በመደገፍ፣ ቀደም ሲል ለነዳጅ ይወጣ የነበረውን ወጪ በመቀነስ፣ የውጭ ምንዛሬ ወጪን በመቆጠብ የሀገርን ሀብት ከወጪ በማዳን የዜጎችን ኑሮ በማቅለል ፤የጉዞ ታሪክ በመቀንስ እንዲሁም የትራንስፖርት አቅርቦትን ችግር በመፍታት፣ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ለውጥ በማምጣት ዋጋን በማረጋጋት እና ለኢንዱስትሪዎችና አምራቾች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የሀገርን እድገት ከፍ ወዳለ ስልጣኔ ማድረስ ያስችላል ።
ከዚህ በተጨማሪ ከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ተርሚናሎችን በተለያዩ የከተማዋ ቦታዎች በመገንባትና ለኤሊክትሪክ ተሽከርካሪዎች ጃርጅ ማድረጊያ ቦታዎችን በየቦታዉ በመገንባት በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ በመቀነስ ህብረተሰቡን ከዝናብና ፀሀይ በመከላከል የትራንስፖርት ፍሰትን በማሳለጥ ፣ የትራፊክ አደጋን መቀነስን ጨምሮ ለዘርፋ የተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን ያመላክታል ።
በቀጣይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ መጨናነቅን በከፍተኛ ደረጃ የሚያቃልሉና የትራንስፖርት ፍሰቱን የሚያሳልጡ የነዋረውን ጊዜ የሚቆጥቡ ተጨማሪ አዳዲስ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ቁጥራቸው 400 የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በዝግጅት ላይ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያዎችን በመገንባት መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በተግባር በማረጋገጥ ላይ ይገኛል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.