የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች የችግር ምንጭ ከመሆ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች የችግር ምንጭ ከመሆን ተላቀው የውበት እና የጤና ምንጭ መሆን ችለዋል!

ከቅርብ አመታት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች ከተማዋን የማይመጥኑ የቆሻሻ መጣያና ማከማቻ የነበሩ በአጠገባቸው ለማለፍ አፍንጫ የሚሰነፍጡና ብዙዎችን ለተለያዩ የጤና ችግር የዳረጉ ነበሩ፡፡ ዛሬ ላይ ይህ ታሪክ ሆኖ አልፏል፡፡ ከተማዋ ወንዞች አክማ ትላንት ከተዘፈቁበት አስከፊ ገጽታ አላቃ የውበት እና የጤና ምንጭ እንዲሆኑ እያደረገች ትገኛለች፡፡

በከተማ አስተዳደሩ በከፍተኛ ትኩረት የሚገነቡት እነዚህ የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ የልማት ፕሮጀክቶች ማራኪ ስፍራዎችን ያካተቱ የተፈጥሮ ሚዛን የጠበቁ፣ አረንጓዴ ስፍራዎችና ውብ የእግር መጓዣ መንገዶችን ያሟሉ ለወጣቶችና ለህፃናት መጫወቻ ሜዳዎችን ያሟሉ ማህበራሰቡ በእግር የሚጓዝባቸው ብሎም ጤናውን የሚጠብቅባቸው እና የጋራ ጊዜ የሚያሳልፍባቸው አዲስ መልክና ዘመናዊ ገፅታን የተላበሱ የከተማዋ የውበትና የደስታ ምንጭ ናቸው፡፡

ለአብነትም በቅርቡ ለከተማችን ተጨማሪ ድምቀት የሆነው እና በቅርቡ ተመርቆ ለህዝብ ክፍት የሆነው የቀጨኔ በአምባሳደር ጊዮን እሬቻ ባምቢስ የወንዝ ዳርቻ ልማት 351 ሄክታር ስፋት ያለው እና 10 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሆኖ የተለያዩ መሰረታዊ ልማቶችና የህዝብ መገልገያዎችን በውስጡ አካቷል፡፡

በተጨማሪም ሌላኛው የከተማዋ ድምቀት የሆነው ከእንጦጦ አንስቶ ቀበና የሚዘልቀው የወንዝ ዳርቻ ልማት በውስጡ አስገራሚና አስደናቂ መሰረተ ልማቶችን አሟልቶ ለነዋሪዎች አዲስ ስሜትን የፈጠረ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት የወንዞችን ህልውና ከመታደግ ባለፈ የከተማዋን ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት አኗኗርና እንቅስቃሴ ያሻሻለ እንዲሁም የከተማዋን የቱሪስት መስህብ በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ተደማሪ ስኬት መሆን የቻለ ነው፡፡

ለሀገር አሳቢ በሆኑ ቅን ልቦች የተገነቡት እነዚህ የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች የማህበረሰቡ ችግር መሆናቸው አብቅቶ ዛሬ ላይ የኢኮኖሚ ምንጭ እና የከተማዋ የቱሪስት ስብሀት በመሆን ለከተማው አዲስ ውበት እና ተጨማሪ ዕድል ፈጥረዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.