የህብረተሰቡን የቤት ችግር ለመቅረፍ በከፍተኛ ት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የህብረተሰቡን የቤት ችግር ለመቅረፍ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራ ነው

አዲሰ አበባ ከተማ የብልጽግና ተምሳሌትነቷን እያረጋገጠች፤የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት እውን እያደረገች፤የከተሜነት ጉዞዋን እያፋጠነች የምትገኘው ከተማችን፤ በመፍጠር እና መፍጠን መርህ በ24/7 የስራ ባህልን በመተግበር፤ ለዜጎች የቤት ልማት አቅርቦትን ለማሳደግ እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ላይ የአቅርቦት እና የአሰራር ለዉጥ በማድረግና የተለያዩ ሞዳሊቲዎችን በመቅረጽ ፤በመንግስት እና በግል አጋርነት፤በበጎ-ፈቃድ፤በግል ባለሀብቶች (በሪልስቴት፣ በግልእና በማህበር አልሚዎች ከቤት ግንባታ ወደ ቤት አቅርቦት መሸጋገር የቻለችው ከተማችን አዲሰ አበባ፤ ለነዋሪዎች የቤት አቅርቦትን በበቂ ሁኔታ ተደራሽ ለማድረግ ቀዳሚ ግብ አድርጋ በመስራት ላይ የምትገን ከተማ ናት፡፡

ከተማዋ ቤቶችን አልምታ ከማቅረብ በሻገር የተገነቡ ቤቶች የህብረተሰቡን ማህበራዊ መሰተጋብር እና አብሮነትን በሚያጠናክሩ አሰራር የተቃኙ በመሆናችው ፣ የጋራ መገልገያዎች ፤የስፖርት ማዘውትሪያ ስፍራዎችን፣ የህፃናት መጫወጫ፣ አከባቢውን ጽዱ እና ወብ በማድረግ የተቀናጀ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትና የጋራ አስተዳዳር እንዲኖራችው ተደርገው በጥንቃቄና በጥራት የተገነቡ በመሆናቸው ለነዎሪዎች ምቹ መሆን ችላለች፡፡

በተለይም ለልማት ተነሺዎች፣ ለተለያዩ ችግሮች ለተጋለጡ ፣ለአካል ጉዳተኞች ፣ ለአገር ባለውለታዎች ቅድሚያ በመስጠት የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ከማድረግ በተጨማሪ ሁሉንም አይነት የቤት አማራጮች በሽያጭ፣ በኪራይ፣ በቁጠባ (በረጅም ጊዜ ክፍያ) እና መክፈል ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያማከለ አካታች የአሰራር ስረዓት በመዘርጋት በመተግብር ላይ ይገኛል፡፡

ይህ ከተማዋ የምታከናወነው ሰው ተኮር ተግባር በዓለም መድረክ ሰሟ ከፍ ብሎ እንዲነሳ ብሎም እውቅናና እና ምስጋን እንዲቸራት አድርጓል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.