በክቡር ዶክተር ዓለማየሁ አረዳ የተፃፈዉ “ምሉዕነት” የተሰኘው መጽሐፍ የግለሰብን ውስጣዊ እድገት ከማኅበረሰብ ጥንካሬ ጋር በማገናኘት፣ አካታች ፖለቲካን፣ የጋራ ብልጽግናንና ባህላዊ ብዝሃነትን የሚያቀናጅ ጥልቅ ሐሳብ ያቀርባል።
ዋናው መልዕክቱም ልዩነታችንን የመለያየት ምክንያት ሳይሆን የጥንካሬ ምንጭ አድርገን፣ በመተማመን፣ በትብብርና በመደመር የጋራ የወደፊት ዕድላችንን በጋራ መገንባት እንዳለብን ያስገነዝባል።
ይህም በመንግሥት ብቻ ሳይሆን፣ በሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነትና ተሳትፎ የሚሳካ ግብ በመሆኑ መጽሐፉ ለሀገራችን የጋራ እውቀትና ለተሻለ ማኅበረሰብ ግንባታ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ እንጠቀምበት።
ልዩነታችንን አክብረን፣ አቅማችንን አቀናጅተን፣ በመደመርና በትብብር የጋራ ብልጽግናን እንገንባ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.