ባለፉት 5 ዓመታት በመዲናችን 496ሺ 971 ቤቶ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ባለፉት 5 ዓመታት በመዲናችን 496ሺ 971 ቤቶች ተገንብተዉ ለነዋሪዎች ማስተላለፍ የተቻለዉ አዲስ የለዉጥ እሳቤን እዉን በማድረግ ነዉ::

ባለፉት 5 ዓመታት በመዲናችን 496ሺ 971 ቤቶች ተገንብተዉ ለነዋሪዎች ማስተላለፍ የተቻለዉ አዲስ የለዉጥ እሳቤን እዉን በማድረግ ነዉ::

የአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር ባለፉት አምስት ዓመታት የነዋሪዎችን መሰረታዊ ፍላጎትና አንገብጋቢ የሆነውን የቤት ችግር በመረዳት አዲስ የለዉጥ እሳቤን እዉን በማድረግ 496ሺ 971 ቤቶች ተገንብተዉ ለነዋሪዎች እንዲተላለፉ አድርጓል ::

 ከተማ አስተዳደሩ በቤት ግንባታ ልማት ሂደት ዉስጥ የመንግስት ሚና ቀዳሚ በማድረግ የተለያዩ የግንባታ አማራጮችን  በመዘርጋት  ቤት አልሚ ሪል እስቴቶች፤የግል አልሚዎች ህብረት ስራ ማህበራት እና በጎ ፈቃደኞች ተቀናጅተዉ  በመኖሪያ ቤት ልማት ዘርፍ ተሳታፊ እንዲሆን ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል፡፡
 
በተለይም ከተማ አስተዳደሩ የአጭር ጊዜ እቅዶችን  በመንደፍና ተግባራዊ በማድረግ ስኬታማ ስራዎችን በመተግበር ላይ ሲሆን በተጨማሪ በዘንድሮው ሩብ አመት ብቻ የመርካቶ በጎነት መንደርን ጨምሮ ከ4 ሺ 200 በላይ ቤቶች በመገንባት ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ተችሏል፡፡
 
እነዚህ የቤት ግንባታዎች ንጹህ የመኖሪያ አካባቢን የፈጠሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ  ምቹ አካባቢ በመፍጠር የልጆች መጫወቻ የተሰራላቸው ሰው የሚንቀሳቅስባቸው አና የእርስ በእርስ ግንኙነት ማጠናከሪያ ስፍራ የተሟላላቸው  የዜጎችን ክብር የሚመጠኑ መኖሪያ መንደሮች ናቸው፡፡   

በአጠቃይ የአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር የልማት ተነሺዎችን፤ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉን፤አረጋዉያንንና የሃገር ባለዉለታዎችንና ሌሎች ቤት ፈላጊዎችን  የቤት ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ  ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል አካታች የሆነ የልማት ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ላይ ይገኛል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.