የታሸጉ ውሀዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ለ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የታሸጉ ውሀዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ከውሀ አምራቾች ማህበር ጋር ስምምነት ተደረሰ።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከውሀ አቅራቢዎች ማህበር አመራሮች ጋር በመዲናችን አዲስ አበባ የታሸጉ ውሀዎች በተመጣጣኝ ዋጋ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በውይይት መድረኩ  ከታሸጉ ውሀዎች አቅርቦት ጋር ተያይዞ ከዋጋና ከጥራት አንፃር የተካሄደ የዳሰሳ ውጤት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

በመድረኩ የውሀ አቅራቢዎች ማህበር አመራሮች የከታሸገ ውሀን ከማምረት ጀምሮ በግብይት ሂደት ይታያሉ ያሏቸውን ችግሮች በተለይም የማምረቻ ጥሬ ዕቃ ላይ ያለውን የደላላ ጣልቃ ገብነት አንስተው በመንግስት በኩል መፍትሄ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የመድረኩን ዓላማ ሲገልፁ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከታሸጉ ውሀዎች ጋር ተያያይዞ የታየውን የዋጋ ጭማሪ ምክንያት ከባለቤቶቹ አንደበት በመስማት የመፍትሄ አቅጣጫ ለመተለም ነው ብለዋል።

#በመጨረሻም ከውሀ ምርት ጋር በተያያዘ ፋብሪካዎች ለአከፋፋዮችና ለቸርቻሪዎች የሚሸጡበትን ዋጋ በየግላቸው ወስነው በማህበራቸው አማካይነት በአጭር ጊዜ ለአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ለማሳወቅ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.