ያልተጣራ ፍሳሽ ወደ ወንዝ የለቀቁ ሁለት የመኪና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ያልተጣራ ፍሳሽ ወደ ወንዝ የለቀቁ ሁለት የመኪና እጥበት ድርጅቶች 800 መቶ ሺህ ብር ተቀጡ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ከአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር  በወረዳው ውስጥ የሚገኙ ሁለት የመኪና እጥበት ድርጅቶች 800 መቶ ሺህ ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱ ገለጸ። 

​ድርጅቶቹ ከመኪና እጥበት የሚወጣውን ያልተጣራ ፍሳሽ ቆሻሻ በቀጥታ ወደ መስመር ቱቦና ወደ ወንዝ በማገናኘት የአካባቢ ብክለት ሲፈጽሙ በመገኘታቸው በደንብ ቁጥር 180 ተራ ቁጥር 6 መሠረት ቅጣቱ ተጥሎባቸዋል። 

በዚህም መሠረት ሚሊኒየም ዘመናዊ የመኪና እና ምንጣፎች እጥበት 400,000 (አራት መቶ ሺህ) ብር እንዲሁም Wash Car 24 Hours የመኪና እጥበት 400,000 (አራት መቶ ሺህ) ብር ተቀጥተዋል። በድምሩ 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) ብር ቅጣት የተጣለባቸው ሲሆን ወደ ወንዝ እና መስመር ቱቦ ተያይዞ የነበረው ህገ-ወጥ ፈሳሽ ማስተላለፊያ መስመር ወዲያውኑ እንዲቋረጥ ተደርጓል። 

​ባለሥልጣኑ ማንኛውም የግልም ሆነ የመንግሥት ተቋም የአካባቢን ንጽህና የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት በማሳሰብ መሰል ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በሚፈጽሙ አካላት ላይ የሚወሰደው አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። 

​ኅብረተሰቡ መሰል የአካባቢ ብክለት እና የደንብ መተላለፍ ሲመለከት በ9995 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.