በአዲስ አበባ ከተማ የሚከናከኑ ኩነቶች እንደአስፈላጊነቱ ዕውቅናና የይለፍ ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ይታወቃል።
የማንኛውም ኩነት ፈቃድ አሰጣጥና የቁስ የይለፍ ፈቃድ ራሱን የቻለ አሰራር ያለው በመሆኑ ፈቃድ ሰጪ ተቋም በራሱ የደብዳቤ ሎጎ በማድረግ የሚሰጥ ነው።
የከተማ አስተዳደሩም ሆነ የኩነት አመቻችና ፈቃድ ሰጪ ቢሮዎች ኩነት ለማዘጋጀት የጠየቀው አካል አሰራርን በጠበቀ መልኩ ባሳወቀው መሰረት የኩነት ማዘጋጀት የሚችልበት ፈቃድና የመኪናና መሰል ጉዳዮች የይለፍ ማረጋገጫ በኩነት ፈቃጁ ተቋም ደብዳቤ የተቋሙ ሎጎ ተደርጎበት ይሰጠዋል።
ነገር ግን ባደረግነው ክትትልና ቁጥጥር ያልተፈቀደላቸው አካላት ህገ ወጥ የይለፍ (Pass) ወረቀት በመያዝ እያጭበረበሩ መሆኑን ደርሰንበታል።
በዚህም የትራፊክ ቁጥጥርን በመጣስ፣ ከመጠን በላይ በፍጥነት በማሽከርከር ፣ ከተፈቀደው መስመር በተቃራኒ በመንዳት፣ የመኪና መለያዎችን ያለአግባብ በመጠቀም ፣ የጥቁር መስታወት ሽፋኖችንና የVIP ፈቃዶችን ያለሕጋዊነት መጠቀምና መሰል የህግ ጥሰቶችን እንደሚያከናውኑ የደረስንበት ሲሆን ይህን ተግባር ለማስቆምና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ብሎም ወንጀለኞችን ለህግ በማቅረብ አስተማሪ እርምጃ እየወሰድን እንገኛለን።
በመሆኑም የከተማችን ነዋሪዎች እንደዚህ አይነት ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ አካላትን በነፃ የስልክ መስመር 8882 እና በሌሎች አማራጮች ጥቆማ እንድትሰጡን እንገልፃለን።
ዘላቂ ሰላም፣ አስተማማኝ ደህንነት ለተምሳሌት ከተማ!!!
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.