"#በቀደመው_ቤታችን ህፃናት ልጆቻችን የመፀዳጃ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"#በቀደመው_ቤታችን ህፃናት ልጆቻችን የመፀዳጃ ቤት አገልግሎት ለማግኘት የሚደርስባቸው ጭንቀት ለከፍተኛ ስነ-ልቦናዊና ጤናታዊ ጉዳት ሲዳርጋቸዉ ነበረ!"፦ አቶ ካሣሁን ዓለሙ _ የቤት ግንባታ ተጠቃሚ

በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ  ተመርቆ ለተጠቃሚዎች የተላለፈዉ የቤት ተጠቃሚ የሆኑት አቶ ካሣሁን ዓለሙ በደስታና በእንባ በተሞላ ስሜት ቀደሞ የነበረውን አስቸጋሪ ህይወታቸውን ያሰታውሳሉ "በቀደመው ቤታችን ህፃናት ልጆቻችን የሽንት ቤት አገልግሎት ለማግኘት የሚደርስባቸው እንግልት ለከፍተኛ ስነ-ልቦናዊና ጤናታዊ ጉዳት ይዳርጋቸው ነበር ማድቤቱም ቢሆን በቆርቆሮ የተጠጋገነ ነበር" ሲሉ የነበረውን ፈተና ያስታውሳሉ አሁን ግን ከነበረበት የትግልና የጭንቅ ህይወት ወጥተው ሰፊ ሳሎን ፣ ዘመናዊ ኩሽና ፣ የሻወርና የዕጅ መታጠቢያ ሲንክ ያሟላ አዲስ መኖሪያ ቤት በማግኘታቸው የልጆቻቸውም ሆነ የቤተሰባቸው የአእምሮ እረፍትና ደስታ መመለሱን አይናቸው እንባ ተሞልቶ ይናገራሉ።

ሌላዋ የአቶ ካሣሁን አለሙ ቤተሰብ የሆኑት ወ/ሮ ዕፁብወርቅ ደምለው የአቶ ካሣሁንንና የቤተሰቦቻቸውን ኑሮ ወደ ሁዋላ መለስ ብለው ሲያስታውሱ " ቤቱ ከዛሬ ነገ በላያቸው ላይ እንዳይፈርስ ሁሌ እሰጋ ነበር " በማለት ያስታውሳሉ ። 

ዛሬ ላይ ያ ሁሉ የፈራረሰ ቤት እና የተጎሳቆለ አካባቢ ሙሉ ለሙሉ ተወግዶ በአደስ መልክ ህንፃ ተገንብቶ ለሰዉ ክብር የሚመጥን ደረጃዉን የጠበቀና የተሟላ ሆኖ በመሰጠቱ የተሰማቸዉን ደስታ በመግለፅ ተግባሩ ለሀሉም ነዋሪዎች ተደራሽ እንዲሆን የመደጋገፍ ባህላችን ይበልጥ ሊጎለብት ይገባል ብለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.