"IMEX America 2026" የማይስ ቱሪዝም...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"IMEX America 2026" የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ በላስ ቬጋስ ኔቫዳ በይፋ ተከፍቷል!

አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችበት "IMEX America 2026" የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ በላስ ቬጋስ፣ ኔቫዳ በደማቅ ሁኔታ ተከፍቷል::

ይህ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ንግድ ኤክስፖ፣ በአለም ቀዳሚ ከሆኑ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ኤክስፖ አንዱ ሲሆን፣ ከ150 በላይ የአለም ሀገራት የተውጣጡ ከ3,700 በላይ ተሳታፊ ድርጅቶችን ተገኝተዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዚህ ታላቅ የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ ላይ በመተሳተፍ የከተማዋን የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዕድሎች እና የቱሪዝም ሀብቶችን ለዓለም እያስተዋወቀ ይገኛል::

አዲስ አበባ ከቅርብ አመታት ወዲህ በርካታ አለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ኮንፍረንሶችን በማስተናገድ በአፍሪካ ግንባር ቀደም ከሆኑ የኮንፍረንስ ቱሪዝም መዳረሻዎች መካከል አንዷ መሆኗን ተከትሎ፣ እንዲህ አይነቱ የቱሪዝም ንግድ ኤክስፖ ይበልጥ የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት ለማስተዋወቅ እና በዘርፉ ካሉት ተዋናዮች ትስስር ለመፍጠር ያግዛል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.