በአለምአቀፍ ደረጃ ምርጥ የተባለውን ተሞክሮ ነው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአለምአቀፍ ደረጃ ምርጥ የተባለውን ተሞክሮ ነው ያገኘነው - የናይጀሪያው ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሺቲማ

ከኢትዮጵያ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም የተገኘው ተሞክሮ በናይጀሪያ የስነምግብ- 774 (Nutrition 774) የተሰኘውን የሥርዓተ ምግብ ኢኒሸቲቭ በተጨባጭ ለመተግበር እንደሚያግዛቸው የናይጀሪያው ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሺቲማ ገለጹ።

የናይጄሪያን ከፍተኛ ልዑክ መርተው ለሦስት ቀናት ‘በሥርዓተ-ምግብ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት’ በሚል መሪ ሃሳብ በኢትዮጵያ ኦፊሴላዊ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ በሚዲያ ረዳታቸው በኩል መግለጫ አውጥተዋል። 

በተሰጠው መግለጫ ከኢትዮጵያ የተገኙት ተግባራዊ ትምህርቶች በሀገራቸው የጀመሩትን ፕሮግራም ከግብ ለማድረስ እንደሚያግዛቸው ተካትቶ ቀርቧል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱና ልዑካቸው በሦስተኛው ቀን የኢትዮጵያ ቆይታቸው በአዲስ አበባ ተገኝተው ልምድ የወሰዱበት የቀዳማይ ልጅነት ልማት ትግበራ ለእነርሱ ኢኒሸቲቭ እውንነት ወደ ተጨባጭ እርምጃ እንደሚያመራቸው በመግለጫው ተጠቁሟል። 

በአዲስ አበባ በዋናነት በቅድመ-መደበኛ ትምህርት፣ በጤና እንክብካቤ፣ በሕፃናት ማቆያ እና በወላጆች ስልጠና ላይ ያተኮረው የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ለናይጄሪያው የልዑካን ቡድን ጠቃሚ ተግባራዊ ትምህርት የተገኘበት እንደሆነ መግለጫውን ይፋ ያደረገው THIS DAY: ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 02/2019 ባሳተመው ገጹ ላይ ይዞ ወጥቷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.