"የሰንደቅ ዓላማ ቀን ክብረ በዓል የምናከብረው ለሥነ ሥርዓት ብቻ ሳይሆን፣ በምንወስደው ቁርጠኝነትና በምንፈጽመው ተግባር እና በምናስመዘግበዉ ስኬት ጭምር ነው።"የአዲስ አበባ ከተማ ምቤ/ት ዋና አፈ-ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር
19ኛዉ የብሔራዊ ሰንደቅ በዓላማ ቀን "ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን!" በሚል መሪ ቃል በአድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ በልዩ ልዩ ሁነቶች ተከብሯል።
በበዓሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር ጨምሮ የከተማዋ የምክር ቤት አባላት ፤የከተማዋ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፤የሀገር ባለዉለታ ጀግኖች አርበኞች፤የፀጥታ መዋቅር አካላት፤ የሀይማኖት አባቶች፤አንጋፋና ወጣት የጥበብ ባለሙያዎች፤ የተለያዩ የተቋማት ሰራተኞች፤ተማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸዉ የህብረተሰብ ተገኝተዋል።
በበዓሉ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የእለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር እንደገለፁት 19ኛዉ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የምናከብረው ለሥነ ሥርዓት ብቻ ሳይሆን፣ በምንወስደው ቁርጠኝነትና በምንፈጽመው ተግባር እና በምናስመዘግበዉ ስኬት ጭምር ነዉ ብለዋል፡፡
አያይዘዉም ዛሬ በዚህ ታላቅ ብሔራዊ በዓል ላይ ተሰብስበን የምናከብረው ለክብር ብቻ ሳይሆን፣ የሀገራችንን ሉዓላዊነትና ነፃነት፣ የጋራ ማንነትና የአንድነት እሴቶቻችንንም ጭምር መሆኑንና ከምልክትነት ባለፈ ለጋራ እሴቶቻችን፣ ለመተሳሰባችንና ለሀገራዊ መግባባታችን ያለውን ትልቅ ትርጉም ያሳያል ሲሉ አፈጉባዔዋ ገልፀዋል፡፡
የብሔራዊ መግባባት መሠረቱም ይህ በመሆኑ የከተማችን እድገትና የሀገራችን ብልጽግና ለማረጋገጥ ሁላችንምበትጋትና በትብብር በጋራ በመሥራት የሰንደቅ ዓላማችንን መልዕክት በተግባር መግለፅ እና ማሳየት ይጠበቅብናል ሲሉ መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም ለሀገራችን ሰላምና ደኅንነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነትና ለሉዓላዊነታችን መጠበቅ ውድ መስዋዕትነት የከፈሉና አሁንም በትጋት እያገለገሉ ያሉ የመከላከያ ሠራዊታችንን፣ የጸጥታ አካላትንና ሌሎችንም የሀገር አገልጋዮች በክብር ስናመሰግን ለሀገር ያላቸው ቁርጠኝነት ለሁላችንም አርአያ መሆኑን በማፅናት ነዉ ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ የፌደራል እና የፖሊስ ማርሽ ባንድ ሀገራዊ ጠዓመ ለዛ ያላቸዉ የተለያዩ ጥበባዊ ስራዎች እንዲሁም ወታደራዊ ትርዒቶች ቀርበዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.