አቶ ተክሌ በዛብህ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው በመመደባቸዉ በክብር ሸኝተናል።
ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ ኃላፊነት ከተማችንን በትጋትና በቁርጠኝነት ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ ተክሌ በዛብህ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው በመመደባቸዉ በክብር ሸኝተናል።
በአዲስ አበባ በነበራቸው የጋራ አመራር፣ የጋራ ጥረትና የጋራ አሻራቸው ሁሌም ይኖራል። ለሰጡት አግልግሎትና ለከተማችን ልማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ከልብ እናመሰግናለን።
በሄዱቡት ሁሉ፣ የአዲስ አበባን ልምድና ተሞክሮ በማስፋት ለበለጠ ስኬትና ውጤት መልካሙን ሁሉ እንመኛለን።መልካም የስራ ጊዜ!
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.