ለከተማችን ላበረከታችሁት አገልግሎት እናመሰግናለን! ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ባለፉት ዓመታት ለአዲስ አበባ በትጋትና በቁርጠኝነት ያገለገላችሁ አመራሮቻችንን፣ ወደ ሌላ አዲስ የኃላፊነት ቦታ በመመደባቸዉ በክብር ሸኝተናል።
በአዲስ አበባ የነበረን የጋራ አመራር፣ የጋራ ጥረትና የጋራ አሻራችን ሁሌም ይኖራል። ለሰጣችሁት አገልግሎት፣ ለከተማችን ልማት ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ ከልብ እናመሰግናለን።
በሄዳችሁበት ሁሉ፣ የአዲስ አበባን ልምድና ተሞክሮ በማስፋት የበለጠ ስኬትና ውጤት እንድታስመዘግቡ እንመኛለን።
እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ አዲስ ኃላፊነት ተረከባችሁ የመጣችሁ አመራሮች፣ እንኳን ደህና መጣችሁ!
አዲሱን የኃላፊነት ምዕራፍ በትጋት፣ በአንድነትና በጋራ አመራር፣ ለአዲስ አበባ ሕዝብ የበለጠ የሚታይ ለውጥና የላቀ ውጤት የምናስመዘግብበት ይሁን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.