የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚከበረውን የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ አስታወቀ፡፡
ነገ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ፡-
👉ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ (22 ወይም ጎላጎል አደባባይ ላይ እና ታች)
👉ከአድዋ ድልድይ ወደ ዘሪሁን ህንፃ እና ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ)
👉ከአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)
👉ከቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ ወደ መስቀል አደባባይ (ወሎ ሠፈር አደባባይ ላይ እና ታች)
👉ከጋዜቦ አደባባይ በደንበል ህንፃ ጀርባ ወደ ፊላሚንጎ እንዲሁም ከጋዜቦ አደባባይ በአዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር መብራት (ጋዜቦ አደባባይ)
👉ከቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት (ቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ መብራት)
👉ከቀድሞው ብርሃን ኢትዮጵያ መስቀለኛ በአዲሱ መንገድ ወደ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን (ብርሃን ኢትዮጵያ መስቀለኛ)
👉ከአፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ)
👉ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አፍሪካ ህብረት መብራት)
👉ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ)
👉ከሜክሲኮ አረቁ ፋብሪካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አረቄ ፋብሪካ መስቀለኛ)
👉ከሰንጋ ተራ 40/60 ቤቶች መገንጠያ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መገንጠያ)
👉ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብሔራዊ ቴአትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)
👉ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትዮሮሎጂ መታጠፊያ)
👉ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኤሚግሬሽን መብራት ( ጥቁር አንበሳ መስቀለኛ)
👉ከጎላ ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኤሚግሬሽን መብራት (ጎላ ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ)
👉ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኤሚግሬሽን መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ)
👉ከንግድ ማተሚያ መታጠፊያ ወደ ፍል ውሃ መስቀለኛ (ንግድ መታጠፊያ)
👉ከፓርላማ መብራት ወደ ውጭ ጉዳይ (ፓርላማ መብራት ላይ)
👉ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ)
ከረፋዱ 4:00 ሠዓት ጀምሮ የሚዘጋ ሲሆን አሽከርካሪዎች አስቀድመው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እያሳሰበ ከንጋቱ 12:00 ሠዓት ጀምሮ በተጠቀሱት መንገዶች ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ ማቆም የተከለከለ መሆኑን አሳስቧል።
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት በ01-11-11-01-11 እና በ990 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
Addis Ababa Police
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.