" እሬቻ ለሀገራዊ መግባባት !! "
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2019 ዓ.ም እሬቻ በዓል "እሬቻ ለሀገራዊ መግባባት !! " በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
በፌስቲቫሉ ላይ ተገኝተው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ
እሬቻ የምስጋና በአል ሲሆን፤ ከክረምት ወደ በጋ ስላሸጋገርከኝ አመሰግናለሁ በማለት ፈጣሪ የሚመሰገንበት የአብሮነትና የወንድማማችነት በአል መሆኑን ገልፀዋል።
እሬቻ ሲከበር ብዝሀ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ በሚያደርግና ባህላዊ ቱውፊቱን በመጠበቅ በሰላም፣ በአብሮነትና በወንድማማችነት መከባበርን መሰረት ባደረገ መልኩ የሚከበር በዓል በመሆኑ ሁላችንም በመከባበር በወንድማማችነት በአሉን በጋራ በማሳለፍ አብሮነታችን አጠናክረን መሄድ ይገባል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በበኩላቸው እሬቻ የሰላምና የምስጋና በዓል በመሆኑ እህትማማችነትና ወንድማማችነት በማጠናከር በአብሮነትና በአንድነት በዓሉን ማክበር ይገባናል ብለዋል።
በዓሉን ስናከብር በእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ፣ በህዝቦች መካከል እህትማማችነትና ወንድማማችነትን የምናጠናክርበት እንዲሆን አሳስበዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ዋቅጋሪ እሬቻ ጥላቻን የሚያርቅ ፍቅርን ፣ እርቅና አንድትን የሚያበረታታ በዓል ነው፤ በማለትም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.