ሁሉም ቀና ቢያስብ፣ ሰው ለሰው ቢፋቀር፣ ሁሉም...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ሁሉም ቀና ቢያስብ፣ ሰው ለሰው ቢፋቀር፣ ሁሉም ቢተባበር የት እንደርስ ነበር!!!

ለዓመታት ነዋሪዎቻችን የጎርፍ እና የእሳት አደጋ ደጋግሞ እየጎበኛቸው በከፍተኛ ሰቀቀን፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ ነበር። 

ዛሬ ግን የዜጎቻችንን ክብር ወደ ጠበቀ ውብ የመኖሪያ ቤትና ስፍራ ተሸጋግረው በደስታ ሲኖሩ ማየት ወደር የሌለው ደስታ ይሰጣል። 
ግን ዋናው ጥያቄ  በሀገራችን ዋና ከተማ  ውስጥ እንዴት ብዙ ዜጎቻችን እንደዛ  አይነት  አስቸጋሪ አኗኗር ውስጥ  ለዓመታት  ኖሩ? ዛሬስ ሁሉም በዚህ ፍጥነት  እየተለወጠ ያለው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡
 
መልሱ ፡- ይህን ስራ  እውን ያደረግነው ብዙ አካላትን በማስተባበርና በመደመር ነው። ከያለበት ያለውን እውቀት፣ ሀብትና ጉልበት ሳንሰስት ደምረናል። የተወሰኑት በፋይናንስ ሲደግፉን፣ ሌሎቹ ደግሞ በእውቀታቸው፣ በጉልበታቸው፣ በዲዛይን እና በግንባታ ስራው ላይ በንቃት በበጎ ፍቃድ ተሳትፈዋል። ነዋሪዎቻችንም  ለተሻለ ልማት  የለውጥን ተስፋ ሰንቀው ትልቅ ትብብር አድርገዋል። 
ይህ ሁሉ ጥረት አንድ ላይ ተደምሮ ትልቅ አቅም በመሆን ይህን የመሰለ የመኖሪያ መንደር እና አካባቢን  ፈጠረ። ቅጠል ተራም ታሪኩ ተቀየረ።

ውድ ወገኖቼ፤ አንድ ላይ ተደምሮ ይህንን አዲስ ሰፈር የፈጠረው መሬት፣ ሰዉም፣ ገንዘቡም፣ እውቀቱም የእኛው ነው። ትርጉሙ አንድ ቦታ ላይ ንፁህ የመኖሪያ ስፍራ ከማግኘት እጅግ የላቀ ነው። ይልቁንም ለጋራ ራእይ እየተባበርን፣ በቅንነት፣ በትጋት እና እውነተኛ አገልጋይነት አብረን ስንሰራ ብዙ ሀብቶቻችን ተደምረው የሁላችንንም የጋራ ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጡ፣ የዜግነትን ክብር የሚያልቁ ፣ አዳዲስ እድል እና ሀብት ይፈጥራሉ። 

ስለዚህ በማንኛውም ነገር በጋራ እንቁም፤ ትብብራችንንም ይበልጥ እናጠናክር። ለበለጠ ሀገራዊ ስኬት በመተማመን አብረን እንትጋ! 

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.