የመስቀል የደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የአዲስ አ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የመስቀል የደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የአዲስ አበባን ገፅታ በሚገነባ መልኩ እንዲከበሩ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል::

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የአዲስ አበባን ገጽታ በሚገነባ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማስተናገድ አቅምን በሚያጎላ መልኩ በድምቀት እንዲከበሩ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል መስከረም 16 እንዲሁም የገዳ ሥርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል በሳምንቱ ቅዳሜ መስከረም 23 በከተማዋ በድምቀት ይከበራል።
 
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ፍሥሐ ጥበቡ በዓላቱን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ በዓላቱን በሰላም ማክበር ከሃይማኖታዊ ሥርዓትነት ባለፈ ለሰላማዊ አብሮነት፣ ለባህል ጥበቃ እና ለሀገራዊ አንድነት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የምናሳይበት አጋጣሚ ነው ብለዋል።

 የ2019 ዓመተ ምህረት የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲያልፉ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከጸጥታ አካላት እና ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በቂ ውይይቶች መደረጋቸውን ገልጸዋል።
 
ምክትል ኃላፊው አያይዘውም ወጣቶች በኃላፊነት መንፈስ የበዓላቱን ሥርዓት በማስተናበር በኩል የየበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። 

ነዋሪዎችም ማንኛውንም አጠራጣሪ ነገር ሲመለከቱ በነፃ የስልክ ቁጥር 8882 ለአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
 
AMN


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.