ከቅጠል ተራ ወደ "የበጎነት መንደር በመርካቶ “
የይቻላል ከፍታን ያላቀ የ4 ወራት አስደማሚ ስኬት!!!
"ጉስቁልና የከተሜነት መገለጫ ሳይሆን ስልጡን ማህበረሰብ የሚኖርበት በመሆኑ በዚህ መርህ ዉስጥ ሆነን ከተማችንን እና የሰዎችን አናኗር እያዘመን እንገኛለን፡፡"
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከንቲባዋ ይህን የተናገሩት ቅጠል ተራ ወደ "በጎነት መንደር" የተቀየረበት የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተዉ ንግግር በአደረጉበት ወቅት ነዉ፡፡
ቅጠል ተራ ወደ በጎነት መንደር ከመቀየሩ በፊት የተነሱት ሱቆችና መንደሮች 131 ብቻ እንደነበሩ፤ የአካባቢዉ ሰዎች ህይወታቸዉ ለአደጋ የተጋለጡበት እና አስከፊ አደጋዎችን በአካል ማየታቸዉን ከንቲባዋ አስታዉሰዉ ጉስቁልና የከተሜነት መገለጫ ሳይሆን ስልጡን ማህበረሰብ የሚኖርበት ጭምር በመሆኑ ቅጠል ተራን ወደ በጎነት መንደር ስንለዉጥ በዚህ መርህ ዉስጥ ሆነን ከተማችንን እና የሰዎችን አኗኗር እያዘመን የምንገኝበት አንዱ ማሳያ ነዉ ብለዋል፡፡
ይህ 9 ህንፃዎች የከተሙበት ስፍራ ከ960 በላይ ቤቶች እና ከ371 በላይ ሱቆች የተገነቡበት እንዲሁም የስራ እድሎች የተፈጠሩበት ሲሆን ፅዱ፤ዉብ፤ምቺ አካባቢ እና ዘመናዊ የዉስጥና የዉጪ አገልግሎቶች የተካተቱበት፤-ንፁህ የመጠጥ ዉሃ፤ዘመናዊ የአስፋልት መንገዶች፤የልጆች መጫወቻዎች፤የስፖርት ማዘዉተሪያዎች ፤ፖሊስ ጣቢያ ጨምሮ ሁሉም የልማት ዉጤቶች የተቀናጁበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩልም "ሃብት አላጣንም ስህተቱ ሃብትን በአግባቡ የለመጠቀም መቻል" መሆኑን የጠቆሙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህን እሳቤ በመቀየር አንድ ሆነን እና ተደምረን የሃብት ብክነትን በማስወገድ ዘመናዊ አኗኗርን እና ፍትሃዊ የሃብት አጠቃቀምን በበጎነት መንደር ማረጋገጥ ችለናል ሲሉ ተናግረዋል፡፤
በመጨረሻም ይህ የተቀናጀ ልማት በመንግስት ብቻ ሳይሆን ማህበረሰባችን ባለዉ አቅም ሁሉ ተሳትፈዉበት የተመዘገበ የጋራ ስኬት መሆኑን እና ትዉልድን ጭምር ታሳቢ ተደርጎ የተሰራበት መሆኑን ገልፀዉ ልማቱን በባለቤትነት መጠበቅ፤ማስተዳደርና ማስተላለፍ ይጠበቅባችኋል በማለት ከምስጋና ጋር መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.