የአደባባይ በዓላት ደምቀው የሚገለጡባት - ውብ አዲስ አበባ !
አሁን ያለንበት ወቅት በርካታ ሃይማኖታዊና ባህላዊ የህዝብ የአደባባይ በዓላት የሚከበሩበት ወቅት ነው።
የአደባባይ ክብረ በዓላት ለህዝቦች ወንድማማችት መጠናከር፣ ለከተማዋ ገፅታ ግንባታ፣ ለቱሪዝም እድገት ያላቸውን አስተዋፅኑ የጎላ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ባለፉት አምስት ዓመታት የታየው ለውጥ የከተማችን ነዋሪዎች እነዚህን በዓላት በምቾት እንዲያከብር ያስቻሉ ናቸው።
ደህንነቱ ለተጠበቀ የህዝብ እንቅስቃሴ ምቹ የሆኑ መንገዶች በስፋት ተገንብተዋል። በዓላቱ ትውፊታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ አደባባዮችና ታሪካዊ ቦታዎች ውብ ሆነው ተገንብተዋል፡፡
የነዋሪዎችን እንቅስቃሴ በቀን ሳይገደብ ያለ ስጋት ሌሊቱንም ጭምር እንዲንቀሳቀስ የከተማዋን ጨለማ ጎዳናዎች ታሪክ ያደረጉ የመንገድ ላይ መብራቶች ተተክለዋል።
የከተማዋ ነዋሪ በበዓላትና በእረፍት ቀናት መንፈሱን የሚያድስባቸው፣ አካላዊ እንቅስቃሴ የሚያደርግባቸው፣ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክርባቸውና የሚዝናናባቸው በርካታ ፓርኮች፣ ፕላዛዎች፣ ፋውንቴኖች፣ ሰው ሰራሽ ሃይቆች፣ ስፖርት ማዘውተሪያዎች ወዘተ ለነዋሪው የተበረከቱ መሰረተ ልማቶች ናቸው፡፡
የአዲስ አበባ ሁለንተናዊ ለውጥ ማጠንጠኛው ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹና ዘመናዊ ማድረግ ነው።
የአዲስ አበባን መሰረታዊ ለውጥ በሁሉም መመዘኛ ለነዋሪው የመጣ ገፀ-በረከት ከመሆኑም ባሻገር የሀገራችንን እና የአህጉራችንን ከተሞች ለውጥ በእጅጉ ያነቃቃ ስኬት ሆኖ ቀጥሏል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.