ዛሬ "በኅብር ቀን" ሀገር በቀል እሴቶቻችንን በተግባር በመጠቀም አብሮነትን፣ መረዳዳትንና ሰው ተኮር ተግባራትን ባህል እያደረግን ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር በሁሉም ወረዳዎች፣ ክፍለከተሞች እና በማዕከል ለከተማችን ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተናል።
ሁልጊዜ እንደምናደርገው ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸው፣ ለማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ፣ ለአረጋውያን፣ ለአቅመ ደካሞች፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰራተኞችን ጨምሮ ከለውጡ ዘመን ጀምረን እርስ በእርስ በመረዳዳት ያለው ለሌለው እንዲያካፍል በማድረግ ማዕድ እናጋራለን ።
ዛሬም ክረምቱን ሙሉ እና በበዓላት ስናጋራ እንደነበረው ሁሉ የማዕድ ብቻ ሳይሆን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ እንኳን አደረሳችሁ በማለት ፍቅራችንን፣ አብሮነታችንን እና አክብሮታችንን ለከተማችን ነዋሪዎች አጋርተናል።
አዲሱን አመት የፍቅር፣ የሰላም፣ በትጋት ሰርተን የምንለወጥበት እንዲሆን እመኛለሁ።
መስጠት አያጎድልም ብለው በከተማችን በሙሉ የምናደርገውን የማዕድ ማጋራት ካላቸው አካፍለው አስተዋፅኦ ላደረጉ ባለሃብቶች፣ ማህበራት፣ ልበቀናዎች ፈጣሪ አምላክ አብዝቶ ይስጣችሁ፤ ከልብ እናመሰግናለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.