ጳጉሜን 3/2018 ዓ.ም
የፅናት ቀን ፤-ለኢትዮጲያ ማንሰራራት መሰረት የሆነዉ ፅናታችን የሉዓላዊነታችን መሰረት ነው!
የኢትዮጵያ ብቸኛ ወር የሆነችው የጳጉሜ ወር በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ሀገራዊ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።
ጳጉሜ 3 "የፅናት ቀን" በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ፤- የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድርን ጨምሮ ከፍተኛ የፖሊስ እና የደንብ ማስከበር አመራሮች የፀጥታ አካላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ መርሀ ግብሮች ተክብሯል፡፡
የፀናች ሀገር መሠረት የተቋማት ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን፣ የህዝብ አንድነት፣ኃላፊነትና ተሳትፎ ሲሆን ፅናት በፈተና ጊዜ አለመሸነፍ፣በችግር ውስጥ ተስፋን መጠበቅና የተጀመረን የለውጥ ጉዞ በጥራት እስከ መጨረሻ መፈፀምና ማስፈጸም ነው።
የዛሬ ፈተና የነገ ድል መሠረት በመሆኑ በጋራ በመተጋገዝ፣ በትዕግስትና በቁርጠኝነት ችግሮችን በመሻገር የተሻለ ነገን መገንባት እንችላለን።
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት የአዲስ አመት መሸጋገሪያ የሆነችው የጳጉሜ ወር ቀናት በተለያዩ ሀገራዊ ድሎችን በሚዘክሩ ስያሜዎች እየተከበሩ እንደሚገኙ ጠቁመዉ ቀደምት አባቶቻችን በአንድነት ቆመው የፀናች ሀገርን እንዳስረከቡን ሁሉ የአሁኑ ትውልድም ሀገርን በሚያፀኑ የልማትና የለውጥ ስራዎች በአንድነት በመቆም የሀገርን ፅናት ማረጋገጥና ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ጀነራሉ አክለውም በዱር በገደሉ ሀገርን ለማፅናት መስዋትነት እየከፈሉ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ታላቅ አክብሮት ሰጥተው ኢትዮጲያ በጀግኖች ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች ብለዋል።
አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ /ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ በበኩላቸዉ ኢትዮጲያውያን ለጋራ ዓላማ በጋራና በፅናት የሚኖሩ ህዝቦች መሆናቸውንና ለዚህም የአድዋ ድል ግንባር ቀደም ተጠቃሽ መሆኑን አንስተው አሁን ላይ ታላቁን የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሀገር እንድንታሰራራና ወደ ብልፅግና ማማ እንድትሄድ የለውጡ መንግስት ከመጣ ጀምሮ ውጤታማ ስራዎች በመስራት የጋራ ድምር ዉጤት እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም እንደ ሀገር የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል ውስጣዊ አንድነታችንን በማጠናከር፤ የይቻላል መንፈስን በማጎልበት፤ድህነትንና ተረጅነትን ታሪክ በማድረግ ኢትዮጲያን አፅንተን እናሻግር ሲሉም መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡
በመርሐግብሩ የፌደራል ፖሊስ ፣ የአዲስ አበባ ፖላስ ፣ የደንብ ማስከበርና የእሳትና አደጋ አባላት የተለያዩ ትርኢቶችና ሀገርና የሚዘክሩ ሁነቶች ተካሂደዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.