ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ እና በተለያዩ መንገዶች ከቦሌ - መገናኛ የቪአይፒ ኮሪደር ልማት አካል የሆነውና ቦሌ ብራስ አካባቢ በሚገኝ የመንገድ መሿለኪያ ውስጥ የተፈጠረውን የውሃ ማቆር ችግር አስመልክቶ የሰጣችሁትን ጥቆማ በአክብሮት ተቀብለናል።
በእርግጥም የሰጣችሁት ጥቆማ ትክክል እና ተገቢነት ያለው ከመሆኑ በተጨማሪ ለከተማችን ልማት ያላችሁን ተቆርቋሪነት እና የኔነት ስሜት ያሳየ በመሆኑ ከልብ እያመሰገንን።
ይህ ያልተጠናቀቀው የምድር ውስጥ መሿለኪያ ቦታ የውሃ ማቆር ችግር ያጋጠመው፤ ቀደም ሲል ስራውን ይዞት ከነበረው ኮንትራክተር ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት የውል መቋረጥ በማጋጠሙ እና የግንባታ መጓተት በመከሰቱ ሲሆን ፤ ይህንን ያልተጠበቀ ችግር በመረዳት ተቋማችን አፋጣኝ መፍትሄ ለመስጠት ሲሰራ ቆይቷል።
በመሆኑም ያልተጠናቀቀውን የመሿለኪያ የምድር ውስጥ ስራ ዳግም ለማስጀመር በፍጥነት የአዲስ ኮንትራት ግዢ ጨረታ በማውጣት ሂደቱ ተጠናቋል።
በመጨረሻም ሀሳባችሁን ለሰጣችሁ እና በኔነት ስሜት ተቆርቋሪነታችሁን ለገለፃችሁ ሁሉ በድጋሚ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ ይህንን የተጓተተ ስራ በማጠናቀቅ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤቱን መልሰን ለእናንተው የምናሳውቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን ።
የከተማችንን ልማት ከነዋሪዎቿ ጋር በመሆን እናፋጥናለን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.