ለነዋሪው እፎይታን የሰጡ የአንድ ማዕከል የገቢያ ማዕከላት በአዳስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኑሮ ውድነት መባባስ መንስኤ የሆኑትን የምርት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የፍጆታ እና የሰብል ምርቶች አቅርቦት ከአርሶ አደሮች፣ ከዮኔን እና ከባለሀብቶች ጋር በማስተሳሰር ምርት ወደ ከተማ በቀጥታ እንዲገባ በማድረግ ሸማቹ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የአንድ ማዕከል የገቢያ ማዕከላትን በተለያዩ ቦታዎች በመገንባት ለህዝብ ጥቅም እያዋለ ይገኛል፡፡
በተለይም በከተማዋ ለዋጋ ንረትና ለንግድ ሚዛን መዛባት ምክንያት የሆኑ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች እና ደላሎች ላይ ህጋዊ እርምጃዎችን በመውሰድ በገበያው ላይ ይታይ የነበረውን የዋጋ ንረት በነዚህ የአንድ ማዕከል የገቢያ ማዕከላት አማካኝነት በማስቀረት ገቢያው እንዲረጋጋ ማድረግ ችሏል ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ ግንባታውን አጠናቆ ለህዝብ ክፍት ያደረገው 7ኛውን የለሚ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ነው ።
በለሚ የአንድ ማዕከል ገቢያ በሸማቹ እና በአምራች መሀከል የቀጥታ ግንኙነት እንዲኖር በማድረግ ማህበረሰቡ ለዕለት ፍጆታ የሚጠቀምባቸውን የሰብል ምርቶች፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ የበርበሬና የቅመማቅመም ምርቶች እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በአንድ ማዕከል መሸመት እንዲችሉ እድል ፈጥሯል ፡፡
በዚህ ሁለገብ የገቢያ ማዕከል የሚቀርቡ ምርቶች ከ15 እስከ 20 በመቶ የዋጋ ቅናሽ የሚሸጥበት፣ ዋጋ የሚያንረውን ህገ ወጥ የደላላ ሰንሰለት በመበጣጠስ ከአምራቹ ያልተቋረጠ ምርት የሚቀርብበትና የነዋሪዎችን የኑሮ ጫና በመረዳት ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የተቻለበት ስኬታማ ስራ ነው።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.