አምራችና ሸማቹ በቀጥታ የሚገናኝባቸው ልዩ የአዲ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አምራችና ሸማቹ በቀጥታ የሚገናኝባቸው ልዩ የአዲስ አመት ባዛሮች በ11 ከፍለ ከተሞች ለህዝብ ክፍት ሆኑ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበዓላት ወቅት የሚከሰተውን የምርት እጥረትና የዋጋ ንረት ለመከላከል አምራቾች ከሸማች ጋር በቀጥታ የሚገናኝባቸው ልዩ የአዲስ አመት ባዘሮችን በ11 ከፍለ ከተሞች በዛሬው ዕለት ለህዝብ ከፍት አድርጓል፡፡
 
አስተዳደሩ በዛሬው ዕለት የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከእሁድ ገበያዎች በተጨማሪ በ11 ክፍለ ከተሞች የበዓል ባዛሮች በይፋ ያስጀመረ ሲሆን ሸማቾች ከትራንስፖርት እንግልት ነፃ በሆነ መልኩ በአቅራቢያቸው ከሚገኙ የሸማቾች ሱቆችና የባዛር ማዕከላት መሰረታዊ የግብርናና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን ጨምሮ እንደ ሽንኩርት፣ ቅቤ፣ እንቁላል፣ ዱቄት፣ ዘይት እና የባልትና ውጤቶች እንዲሁም የሀገር ባህልና ዘመናዊ አልባሳትና የተለያዩ ጌጣጌጦች፣ የእደ ጥበብ ውጤቶች እና ልዩ ልዩ የፅዳት ዕቃዎች በስፋት ቀርበዋል።
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የክፍለ ከተሞቹ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የ በዛሬው ዕለት  የተከፈቱትን ባዛሮች በስፍራው በመገኙት በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን፤ ዛሬ ከተከፈተው ልዩ የአዲስ ዓመት ባዛሮች በተጨማሪ በከተማዋ በሚገኙ  የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ላይ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚው በቀጥታ እየቀረበ ይገኛል፡፡
 
እነዚህ የዘመን መለወጫ በዓል ልዩ ባዛሮች ከዛሬ ነሀሴ 28 ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም ድረስ በድምቀት የሚቆይ ሲሆን ነዋሪዎች ወደ ባዛሩ እና ወደ በገቢያ ማእከላት እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ገቢያ በመምጣት የቀረቡትን ሰፊ የገበያ አማራጮች በመጠቀም ተመጣጣኝ እና ጥራት ያለው ግብዓት መሸመት እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.