በካናዳ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የታዳጊ ስፖርት አካዳሚ አባላት በአዲስ አበባ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎበኙ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞው ተጫዋች በሆነው አሸናፊ ግርማ የሚመራው ይህ የልዑካን ቡድን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች የሀገራቸውን ባህል፣ ታሪክና የተፈጥሮ ጸጋ በቅርበት እንዲያውቁ የሚያግዝና የሀገርን በጎ ገጽታ ከመገንባት ባለፈ የስፖርት ቱሪዝም ዘርፍን ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት እና አስተባባሪዎች እንዲሁም የታዳጊዎቹ ቤተሰቦች በተፈጠረላቸው የትውልድ ሀገራቸውን የመጎብኘት እድል መደሰታቸውን ገልጸው በተለይ በአዲስ አበባ ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ እና ፈጣን እድገት መደመማቸውን ተናግረዋል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.