ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ! ከንቲባ አዳነች...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በተለያየ ማህበራዊ ችግር ውስጥ የነበሩ  በየለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በ5ኛ ዙር የክህሎት እና የስብዕና ግንባታ የሰለጠኑ 858  እህቶቻችንን አስመርቀን ወደ ስራ አሰማርተናል።
 
በከተማችን ከምንሰራቸው ሰው ተኮር ስራዎች  አንዱ ትላንት በጎዳና፣ በችግር እና በተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች ውስጥ የነበሩ ሴቶችን  በሙያ ክህሎትና ስብዕና ገንብተን ከነበሩበት አስከፊ ህይወት በማውጣት  ወደ ተሻለ ህይወት  የምናሰማራበት ቀዳሚው ተግባር ነው።
 
አዲስ አበባችን ማህበራዊ ፍትህ የሰፈነባት እንዲሁም ለዘመናት የከረሙ ስብራቶቿ የሚጠገኑባት ከተማ የማድረግ የተግባር ውጤት ፍሬ ማሳያዎች ከለነገዋ ተመርቀው አዲስ ህይወት እየመሩ ያሉት ሴቶች እህቶቻችን  ናቸው።
 
የዛሬዎቹ ተመራቂዎችን ጨምሮ በማዕከሉ በድምሩ 3259 ሰልጣኞችን አስመርቀን ወደ ስራው ዓለም እንዲቀላቀሉ በማድረግ ህይወታቸውን በተሻለ መንገድ እንዲመሩና ለሌሎችም አርዓያ እንዲሆኑ አድርገናል።
 
ውድ ተመራቂዎች፤ አስከፊውን ትላንታችሁን አልፋችሁ፤ በማዕከሉ በነበራችሁ ቆይታ በቀሰማችሁት ክህሎት እና ባገኛችሁት የተሀድሶ ስልጠና ዛሬ ማሸነፍ ችላችኋል፤ ነገም በስራው ዓለም ስኬታማ ለመሆን የሚገጥማችሁን ማንኛውንም ፈተና አሸንፉችሁ  ህይወታችሁን ይበልጥ ብሩህ እንደምታደርጉ እናምናለን።
 
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! 
 
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.