እንበርታ!! ከተማችንን በአብሮነት እናልብስ!

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

እንበርታ!! ከተማችንን በአብሮነት እናልብስ!

በዛሬው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር፣ ከተማችን አዲስ አበባ 1 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅዳ ማልዳ የተነሳች ሲሆን፣ የከተማችን ነዋሪ “ተስፋን መትከል የሁላችን ዋነኛ ሀላፊነት ነው!” በሚል ስሜት ባሳየው ጠንካራ ርብርብ እስካሁን ከዕቅዳችን በላይ 1.4 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ባለቤትነቱን በተግባር አሳይቷል።

አሁንም ቢሆን መላው የከተማችን ነዋሪዎች ይህንን የጀመርነውን እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ ርብርባችንን በማስቀጠል፤ የከተማችንን ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪካዊ አሻራ ማኖራችንን ጠንክረን እንቀጥል፣ እንበርታ እላለሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.