በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል መርሐ ግብር በይፋ ተጀምሯል

በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታሪካዊ መርሐ ግብር በይፋ መጀመሩን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ አብሥረዋል።

ሚኒስትሯ በመግለጫቸው እንዳሉት ኢትዮጵያውያን እንደተለመደው ታሪክ ይሠራሉ።

ኑ ተስፋን እንትከል ሲሉ ጥሪ ያቀረቡት ሚኒስትሯ፣ ዛሬ ታሪካዊ በሆነችው ቀን ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል መሬትን ይዳስሳሉ፣ መሬትም ቃሏን የምታፀናበት ነው ብለዋል።

800 ሚሊዮን ችግኞች፣ በተግባር እና በሐሳብ አንድነት በመደመር ዕሳቤ እናሳካለንም ብለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.