የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ፤ ለትውልድ የሚሻገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ!
የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ የደን ሽፋንን ለመጨመር እና አካባቢን ለመጠበቅ በኢትዮጵያ በሀገር ደረጃ የሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ለትውልድ የሚሻገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ፕሮግራም ነው፡፡ በመርሃ ግብሩ ሚሊዮኖችን በማሳተፍ ቢሊዮኖች ዛፎችን መትከል ተችሏል፡፡ በፕሮግራሙ አካባቢን መጠበቅ፥ የአፈር መሸርሸርን መቀነስ ፥ የተራቆቱ መሬቶችን ማልማት፡ የውሃ ምንጮች እንዲጎለብቱ እና የአረንጓዴ ሽፋን በማሳደግ ተስማሚ ምህዳር እንዲፈጠር ማድረግ ተችሏል።
በከተማችንም ከ2011 ዓ.ም እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ ነዋሪው በየዓመቱ በነቂስ በመውጣት ከ90 ሚሊዮን በላይ የጥላ ዛፎች፤ የውበትና የፍራፍሬ እፅዋት ተተክለዋል፡፡ በከተማችን በተሰራው የአረንጓዴ ልማት ስራዎች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከመጀመሩ በፊት የነበረውን የከተማችን የአረንጓዴ ሽፋን ከ 2.8% ወደ 24% ማሳደግ ተችሏል። በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በከተማችን በየዓመቱ በሚሊዮኖች ችግኞች ተተክለዋል፡፡
በ2011 ዓ.ም 6,084,371
በ2012 ዓ.ም 8,511,531
በ2013 ዓ.ም 11,445,961
በ2014 ዓ.ም 14,795,585
በ2015 ዓ.ም 17,445,385
በ2016 ዓ.ም 26,720,918
በ2017 ዓ.ም 5,644,620 ችግኞች ተተክለዋል።
በአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ ዘመቻም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ችግኞች ተተክለዋል።
በከተማችን አዲስ አበባ በአንድ ጀንበር መርሃ ግብሮች ከ2011 እስከ 2018 ዓ.ም ብቻ በድምሩ 17.6 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል።
በከተማችን በአንድ ጀንበር መርሃ ግብር፡
በ2011 ዓ.ም 1 ሚሊዮን
በ2012 ዓ.ም 2 ሚሊዮን
በ2013 ዓ.ም 1 ሚሊዮን
በ2014 ዓ.ም 4 ሚሊዮን
2015 ዓ.ም 3 ሚሊዮን
2016 ዓ.ም 4.5 ሚሊዮን
2017 ዓ.ም 1.1 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል፡፡
ነገ ሃምሌ 27/2018 ዓ.ም በአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በከተማችን ከ1 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል፡፡
በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ትኩረቱ ከብዛት ባልተናነሰ በጥራት፣ በአገር በቀል ዛፎች፣ በከተማ ውበትና በኮሪደር ልማት ለተዘጋጁ ቦታዎች ተስማሚ የሆኑ ችግኞችን መትከል ላይ በማተኮር የአረንጓዴ ልማት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ህብረተሰቡ በባለቤትነት ስሜት በየዓመቱ በስፋት እየተሳተፈ በሚሊዮኖች ችግኞችን ይተክላል፣ የተተከሉ ችግኞች እንዲፀድቁም የእንክብካቤ ስራዎችን ያከናውናል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.