የ6ኛው ዓመታዊ የወጣቶች የዲፕሎማሲ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የአዲስ አበባን የቱሪዝም መዳረሻዎችና የልማት ስራዎችን ጎበኙ
የ6ኛው ዓመታዊ የወጣቶች የዲፕሎማሲ ኮንፈረንስ እና በሞዴል የዲፕሎማሲ ሲሙሌሽን መርሀ ግብር ለመሳተፍ ወደ የአዲስ አበባ የመጡ ተሳታፊዎች፣ በከተማዋ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም በአዲስ አበባ ከተማ በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች መደነቃቸውን ገልፀው፣ ይህም ለሌሎች ሀገራት ትልቅ ተሞክሮ እንደሚሆን ተናግረዋል::
ይህ አለማቀፍ ጉባኤ፣ ወጣቶችን ለዲፕሎማሲ፣ ለአመራር፣ ለፖሊሲ ጥናትና ለዓለም አቀፍ ግንኙነት የሚያዘጋጅ የልምድ ልውውጥ መድረክ መሆኑ ተገልጿል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.