“ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለጉባዔው ተሳታፊዎች የሎ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለጉባዔው ተሳታፊዎች የሎጂስቲክስ እገዛ አድርገውልናል” መሥፍን አርዓያ (ፕ/ር)

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ተሳታፊዎች የሎጂስቲክስ ድጋፍ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርዓያ (ፕ/ር) ተናገሩ፡፡

የምክክር ጉባዔውን ሂደት አስመልክቶ ዋና ኮሚሽነሩ በሰጡት መግለጫ፤ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉባዔው እየተሳተፉ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች ምክክር በሚደረግበት አቅራቢያ የማረፊያ ስፍራ ሰጥተውልናል ብለዋል፡፡

ለአዲስ አበባ ተሳታፊዎችም ክረምት እንደመሆኑ መጠን በተለይም ከሩቅ ለሚመጡት እገዛ እንዲያደርጉልን ጠይቀን እያገዙን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ ለተመካካሪዎች ትራንስፖርትን ጨምሮ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተሳታፊዎች የሚጠበቅበትን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.