ዛሬ ከሰዎች ለሰዎች ድርጅት ጋር በመተባበር...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ከሰዎች ለሰዎች ድርጅት ጋር በመተባበር በሀገራችን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የስማርት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግንባታ አስጀምረናል።

ይህ ስማርት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግንባታው ሲጠናቀቅ ወጣቶችን  በማኑፋክቸሪንግ፣ በአውቶሞቲቭ፣ በኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ፣ በኮሚዩኒኬሽንስ፣ በቴክስታይል እና የሲኤንሲ (CNC) ቴክኖሎጂዎች ላይ ተግባር ላይ ያተኮረ እና  ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም  ስልጠና ይሰጣል።
 
ሀገርን ማልማት እና ከድህነት መላቀቅ  በንድፈ ሃሳብ ብቻ በተገደቡ ትምህርቶች ማሳካት ስለማይቻል፣ ሃሳብን የሚያፈልቁ አዕምሮዎችን እና የሚሰሩ እጆችን  ያጣመረ  ክህሎት መር የሰው ሀይል እጅግ አስፈላጊ ናቸው።
 
ዛሬ ያስጀመርነው ፕሮጀክት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ወጣቶቻችንን ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት፣ ከንድፈ ሃሳብ ወደ ተግባር የሚያሸጋግር፣  አዲስ የሥራ እድል የሚፈጥር የክህሎት ድልድይ የሚሆን ነው። 
 
የዚህ ኮሌጅ ግንባታ በጥራትና በተቀመጠለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ  በልዩ ትኩረት የምንከታተለው  ሲሆን፣  ፕሮጀክቱን በትብብር የሚገነባው የረጅም ጊዜ የልማት አጋር የሆነው ሰዎች ለሰዎች ድርጅት እና የሚሰራው ለትውልድ የሚሻገር  አሻራ ነው ብላችሁ መሬታችሁን ለፕሮጀክቱ የለቀቃችሁ አርሶ አደሮችን  በራሴና  በተጠቃሚ ወጣቶች ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ። 
 
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.