"ታላቅ ትዉልድ እና ታላቅ ታሪክ ካላት ታላቅ ሀ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ታላቅ ትዉልድ እና ታላቅ ታሪክ ካላት ታላቅ ሀገር በመወለዴ ኩራት ተሰምቶኛል፣ ያረጋገጥኩት እዉነታም ይኸዉ ነዉ።" ትዉልደ ኢትዮጵያዊዉ ዓሊ አሕመድ

ትዉልደ ኢትዮጵያዊው የካናዳ ብሔራዊ ቡድን የእግር ኳስ ተጨዋች ዓሊ አሕመድ የዓድዋ ድል መታሰብያ ሙዝየምን ጨምሮ፣ የወንዝ እና ወንዝ ዳርቻ ልማት (መቀጠያ፣ አራዳ ፓርክ እና ቀበና)፣ የስፖርት ማዘውተርያ መሰረተ ልማት ጎበኘ። 

“ታላቅ ትዉልድ፣ ታላቅ ታሪክ ካላት ሀገር በመወለዴ ኩራት ተሰምቶኛል፤ በዓድዋ ድል መታሰብያ ሙዝየም ተገኝቼ  ያረጋገጥኩትም ይኸዉ ነዉ” ያለዉ ዓሊ አሕመድ፥ “ሌሎች አፍሪካዉያን ሊማሩበት እና ልምድ ሊወስዱበት የሚገባ ነዉ” ብሏል፡፡

አያይዞም ፥ ወደ ኢትዮጵያ የመጣበት ዋነኛ ዓላማ ታዳጊዎችን ለማነቃቃትና የኢትዮጵያን የእግር ኳስ ዕድገት ለመደገፍ እንደሆነ ገልፆ? ኢትዮጵያ ነፃነቷ በመቀዳጀት ያረጋገጠችዉን ሉዓላዊነት እና ፈጣን እድገት በስፖርቱም ዘርፍ እንድትደግም ምኞቱ መሆኑን በሰጠዉ ምላሽ ጠቁሟል፡፡

ለዚህም አዲስ አበባ ከተማ ለዘመናዊ ስፖርት ዕድገት እየሠጠች ያለዉን ትኩረት የሚደነቅና ለመጪዉ ትዉልድ መሠረት የጣለ በመሆኑ ትዉልዱ ሊጠቀምበት ይገባል ሲል ገልፃል፡፡ እንዲሁም የከተማዋ ሁለንተናዊ እና አካታች ዕድገት ተዘዋውሮ መመልከቱ እንዳስደነቀው ተናግሯል። 

በመጨረሻም የኢትዮጵያዉያን ልዩ እንግዳ አቀባበል እና ባህል አድንቆ፥ ልባዊ ምስጋናዉን አቅርቧል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.